አዘክሪ ድንግል አዘክሪ!
ኀዳር ፭፤፳፻፲፰ ዓመተ ምሕረት
አዘክሪ ድንግል አዘክሪ
ለልጅሽ አሳስቢ አዘክሪ
ለኃጥአን ለምኝልን
አይደለም ለጻድቃን
ከጠላት ሸሽተሽ ለተሰደድሽበት
በግብጽ በረኀ በሙቀቱ ውዕያት
በዱር በገደሉ በቁር ግሽበት
በጀርባዎችሽ አዝለሽ ለተጓዝሽበት
በመታቸው ተረከዞች እንቅፋት
ያን ሁሉ መከራ ለተቀበልሽበት
ለማዳን ሰውን ከጽኑ ግርፋት
ከሲኦል ትላትል ቁንጥጫ ከገሃነመ እሳት
ለአዳም ዘር በሙሉ የነፍስ ድኅነት
ለምኝልን እናት አትተይን በእውነት
አዘክሪ ድንግል አዘክሪ
ለልጅሽ አሳስቢ አዘክሪ!
