[smartslider3 slider="3"]

“ሰው ችግሩን በልቡ እያወቀ በዓይኑ እያየ እንዴት ገደል ውስጥ ይገባል? ዕርቅና ይቅርታ ማንን ጐዳ? ሰላምና አንድነት ማንን አከሰረ? ሰበብ አስባብ እየተፈለገ በሆነውም ባልሆነውም ከመተላለቅ ለምን ኢትዮጵያ የሁላችን ናት ብለን በእኩልነትና በስምምነት መኖር አቃተን?”

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በዓለ ልደትን አስመልክቶ ለመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ያስተላለፉት መልእክት።

መልካም አስተዳደር እና ቤተ ክርስቲያን

የእግዚአብሔር ቤተ ሰቦች! እንዴት ሰነበታችሁ? በክፍል ሁለት ጽሑፋችን ‹‹የቤተ ክርስቲያን መልካም አስተዳደር እጦት መንሥኤዎች›› በሚለው ርእስ ከተራ ቁጥር አንድ እስከ አምስት የዘረዘርናቸውን ምክንያቶች ታስታውሳላችሁ፡፡ በዚህ ክፍልም ከዚያው የቀጠለውን ይዘንላችሁ ቀርበናል፤ መልካም ንባብ!

መልካም አስተዳደር እና ቤተ ክርስቲያን

መልካም አስተዳደር ምን ማለት እንደ ሆነ ከዚህ በፊት ባቀረብነው ክፍለ ትምህርት ለመግለጽ ሞክረናል፡፡ ለቤተ ክርስቲያን አስፈላጊ መሆኑ እንደማያጠያይቅም ተመልክተናል፡፡ ይሁን እንጂ ቤተ ክርስቲያናችንን ከገጠር እስከ ከተማ፣ ከመመሪያ እስከ አጥቢያ የመልካም አስተዳደር እጦት በእጅጉ እየፈተናት መሆኑን በርካታ አካላት ይገልጻሉ፡፡