በማኅበረ ቅዱሳን የሚተላለፈው ቴሌቪዥን ዝግጅት የሰዓት ለውጥ ተደረገ
መጋቢት 25 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በማኅበረ ቅዱሳን የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ዝግጅት ክፍል እየተዘጋጀ በNilesat/EBS የሚቀርበው የ30 ደቂቃ መርሐ ግብር በየሳምንቱ እሑድ ከጧቱ 3፡30-4፡00 ሲተላለፍ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ሰዓቱ በቅዳሴ መጠናቀቂያ ላይ ይተላለፍ ስለነበር ለመከታተል አስቻጋሪ እንደሆነ ለክፍሉ ከሚደርሱት መልእክቶች ለመረዳት ተችሏል፡፡
በዚህም መሠረት ከፊታችን እሑድ ከመጋቢት 28 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ በየሳምንቱ እሑድ ከቀኑ 5፡30-6፡00 ሰዓት የሚተላለፍ መሆኑንና የተላለፉ መርሐ ግብሮችን eotc.tv ላይ እንዲሁም በyoutube ላይ Mahibere kidusan Tv Program ብሎ በመፈለግ ማግኘት እንደሚቻል የሬድዮና ቴሌቪዥን ክፍሉ አስተባባሪ የሆኑት ዲ/ን ሄኖክ ኀይሌ ገልጸዋል፡፡