‹‹ሙሴ ሆይ፥ እነሆ በውስጥም በውጭም ሁለመናህ ነጭ ሆነ››

ሰዎች ከገድሉ የተነሣ የሚያደንቁት ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አባት አባ ሙሴ ጸሊም አስቀድሞ ለሥጋው የሚኖር ወንበዴና አመንዛሪ እንዲሁም ቀማኛ ነበር፡፡ እንዲያውም የሥጋውን መሻት ለመፈጸም ሰዎችን እስከ መግደል የሚደርስ ጨካኝ ሰው እንደነበር ገድሉ ይናገራል፡፡ መብልንና መጠጥንም ከልክ ባለፈ መልኩ ይወስዳል። መጽሐፈ ስንክሳር ላይ እንደተመዘገበው በአንድ ጊዜ አንድ ሙሉ በግ እና አንድ ፊቅን ወይን ጠጅ እንደሚጨርስ እራሱ ይናገር ነበር፡፡

‹‹ከአንተ በፊትም ከአንተ በኋላም የሚመስልህ የለም›› (፩ኛነገ.፫፥፲፪)

የጠቢቡ ሰሎሞን ጥብብ መደነቅና ተሰሚነት በሰዎች ዘንድ ብቻ አልነበረም፤ ‹‹አራዊትና ወፎች ሁሉ ወደ እርሱ ይመጡ፣ ቃሉን ይሰሙ፣ ጥበቡንም ያደንቁ፣ ከእርሱ ጋር ይነገጋሩና ወደ ሥፍራቸው ይመለሱ ነበር፡፡››

‹‹ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ›› (ማቴ. ፲፮፥፲፰)

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? ትምህርት እንዴት ነው? የዓመቱ የትምህርት ወቅት እየተገባደደ የፈተና ጊዜ ደርሶ እየተፈተናችሁ ያላችሁ ተማሪዎች አላችሁና ፈተና እንዴት ነው? መቼም በደንብ እንዳጠናችሁ ተስፋችን እሙን ነው! ወደፊት መሆን የምትፈልጉትን ለመሆን በትምህርታችሁ ጎበዝ መሆን አለባችሁ!

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ለዛሬ ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትርጉምና በመጀመሪያ ስለታነጸው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በጥቂቱ እንነግራችኋለን፤ መልካም ቆይታ!

የቅዱሳንን ገድል የመማር አስፈላጊነት

የቅዱሳንን ገድል ለምን እንደምንማር ለማወቅ ቅዱሳት መጻሕፍት ላይ የተጠቀሱትን ታሪኮች ምሳሌ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ በቃሉ የተናገረላቸው ቅዱሳን ስለመኖራቸው በቀዳሚነት መጽሐፍ ቅዱስ ተጠቃሽ ነው፡፡

ንዑስ አገባብ

ውድ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? የእግዚአብሔር አምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን! ባለፈው የትምህርታችን ክፍለ ጊዜ ላይ ‹‹ደቂቅ አገባብ›› በሚል ርእስ አስተምረናችሁ ነበር፡፡ በዚህ ሳምንት ደግሞ ለሰጠናችሁ መልመጃ ምላሽና ስለ ‹‹ንዑስ አገባብ›› እንመለከታለን፤ በጥሞና ተከታተሉን!

በዓለ ቅዱስ ሚካኤል

በእስክንድርያ ከተማ ክላወባጥራ የተባለች ንግሥት የበጥሊሙስ ልጅ ዙሐል በሚባል ኮከብ ስም ያሠራችው ታላቅ ምኲራብ ነበር፤ ሕዝቡም ሰኔ በገባ በዐሥራ ሁለት የዚህን ጣዖት በዓል ያከብሩ ነበር። ይህንም ግብራቸው እንዲተው አባታችን እለ እስክንድሮስ ቢነግራቸው አይሆንም አሉት።…

ቅዱስ ላሊበላ

ቅዱስ ላሊበላ ከአባቱ ዣን ስዩምና ከእናቱ ኪርወርና በታኅሣሥ ፴፱፣ ፲፻፩ ዓ.ም በላስታ ቡግና ወረዳ ልዩ ስሟ ሮሀ በተባለችው ሥፍራ ተወለደ፡፡ አባቱ በላስታ አውራጃ የቡግናው ገዢ ነበር፤ እናቱ ደግሞ አገልጋይ ነበረች፡፡ የልደቱን ነገር አስቀድሞ ቅዱስ ሚካኤል ለእናቱ ነግሯት ነበር፤ ቅዱስ ላሊበላ በተወለደ ጊዜም ብዙ ነጫጭ ንቦች መጥተው በሰውነቱ ላይ አርፈው እንደ ማር እየላሱት ስለታዩ እናቱ ‹‹ልጄን ንብ ዘበኛ ሆኖ ይጠብቅልኛል›› ስትል ስሙን ‹‹ላል ይበላል›› ብላዋለች፡፡ ‹ላል› በአገውኛ ‹ንብ› ማለት ነው፡፡ በጊዜ ብዛት በተለምዶ ነው ‹‹ላሊበላ›› ተብሎ መጠራት ተጀመረ፡፡ ንቦቹ ግን ሥጋዊ ንቦች ሳይሆኑ በንብ የተመሰሉ መላእክት ናቸው፡፡ ንጉሥ መሆኑን እያመለከቱ ሃይማኖትና ምግባር ማር ከእርሱ እንደሚቀዳ ለማመልከት በንብ ሠራዊት ተመስለው ሰውነቱን ላሱት፡፡

ቅዱስ ገላውዴዎስ

የሮሙ ንጉሥ የኑማርያኖስ ወንድም ከሆነው አባቱ አብጥልዎስ የተወለደው ገላውዴዎስ የመላእክት አርአያ የተባለ ቅዱስ ነው፡፡ የአንጾኪያ ሰዎችም አባቱን እጅግ ይመኩበትና ይወዱት ነበረ፤ በሕይወት እያለም በጦርነት ድል ሲያደርግ የሚያሳይ ሥዕሉን በከተማው ላይ አሠርተው ያከብሩት ነበር፤ ልጁ ቅዱስ ገላውዴዎስ ግን የቤተ ክርስቲያንን ቅዱሳት መጻሕፍትን ዘወትር ያነብ ነበር፡፡

ነቢዩ ሳሙኤል

ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ወገን ከሆኑት ከአባቱ ሕልቅና እና ከእናቱ ሐና የተወለደው  ሳሙኤል የእግዚአብሔር ነቢይ እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠቅሳሉ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ተጽፏል፤ ‹‹ሕልቅናና ሐናም ማልደው ተነሥተው ለእግዚአብሔር ሰግደው ሄዱ፤ወደ ቤታችውም ወደ አርማቴም ደረሱ፤ ሕልቅናም ሚስቱን ሐናን ዐወቃት፤ እግዚአብሔርም አሰባት፤ ፀነሰችም፡፡ የመውለጃዋም ወራት በደረሰ ጊዜ ሐና ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርስዋም ‹‹ከሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለምኜዋለሁ›› ስትል ስሙን ‹ሳሙኤል› ብላ ጠራችው፡፡›› (፩ኛሳሙ.፩፥፲፱-፳)

‹‹ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምሕላ፤ ጾምን ለዩ! ምሕላንም ዐውጁ›› (ኢዮ.፩፥፲፬)

የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተገልጦ ፍርሃትና ሥጋታቸው የተወገደላቸው ቅዱሳን ሐዋርያት ለወንጌል አገልግሎት ከመሠማራታቸው በፊትና ሕገ ወንጌልን ከማስተማራቸው አስቀድሞ አገልግሎታቸው እንዲቃና፣ መንፈስ ቅዱስ እንዳይለያቸውና የመንፈስ ቅዱስን ምሪትና ኃይል ለመቀበል ሱባኤ ያዙ፤ ሀብተ መንፈስ ቅዱስም በአገልግሎታቸው እንደሚበዛ ሲያረጋግጡ ቅዱሱን ወንጌል የሚያገለግሉበትን ክፍለ ዓለም ዕጣ በመጣጣል ዕጣው ወደ ደረሳቸው የአገልግሎት ቦታ መሰማራታቸውን የቤተ ክርስቲያን የታሪክ መዛግብትና ሊቃውንት አባቶቻችን ያስረዳሉ::