ርእዮ ለይብኪ ዐይነ ልብ ዘቦ (ሰቈቃወ ድንግል)

አባ ጽጌ ድንግል ይህን ቃል የተናገረው የቅድስት ድንግል ማርያምን ስደቷን፣ በስደቷ ጊዜም የደረሰባትን መከራና ኃዘን አምልቶ በገለጸበትና አምላክን በኅቱም ድንግልና ፀንሳ በኅቱም ድንግልና የወለደች ድንግል ማርያምን ባመሰገነበት ክፍሉ ነው። ሙሉ ቃሉን እንደሚከተለው እንመልከተው።…

ምኞት

ሰው አንድን ነገር የራስ ለማድረግ በብርቱ ፍላጎት ወይንም ምኞት ይነሣሣል፤ በመልካም ምኞቱ የነፍስ ፍላጎትን ሲፈጽም የሥጋዊው ግን ወደ ጥፋት ይመራዋል፡፡ ሥጋዊ ምኞት በመጀመሪያ ጊዜያዊ ደስታን ቢሰጥም ፍጻሜው ግን መራራ ኅዘንን የሚያስከትል ነው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞንም ይህን በምሳሌው እንዲህ ሲል ገልጾታል፤ ‹‹የጻድቃን ምኞት መልካም ነው፤ የኃጥአን ተስፋ ግን መቅሠፍት ነው›› (ምሳሌ. ፲፩፥፳፫)

‹‹እመን እንጂ አትፍራ›› (ማር. ፭፥፴፮)

የደኅነታችን መሠረት እምነት በክርስቲያናዊ ሕይወታችን ውስጥ ችግርና መከራ በበዛብን ጊዜ ጸንተን እንድናለፍ ይረዳናል፡፡ የሰው ዘር በኃጢአቱ የተነሣ በምድር እንዲኖር ከተፈረደበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ ችግርና መከራ ተይዞ ሲሠቃይ ፈጣሪውን ያስባል፤ ይማጸናልም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፈውስን ሲያገኝ በሌላ ጊዜ ግን ወደማይመለስበት ዓለም በሞት ይለያል፤ ሆኖም ድኅነተ ሥጋንም ሆነ ድኅነተ ነፍስን ከአምላካችን እናገኝ ዘንድ እምነት ያስፈልጋል፡፡

‹‹የሞተ ሰውስ ዐረፈ፤ ነገር ግን መታሰቢያውን አድርግለት›› (ሲራክ ፴፰፥፳፫)

ሰዎች ሕያው ሆነን በፈጣሪ አምሳል እንደተፈጠርነው ሁሉ በኃጢአት ሳቢያ የተፈረደበትንን ሥጋዊ ሞት እንሞት ዘንድ አይቀሬ ነው፤ ‹‹አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህና›› እንደተባለውም የሰው ዘር በሙሉ ወደ አፈርነት ይመለሳል፡፡ በሕፃንነትም ይሁን በጎልማሳነት እንዲሁም በእርጅና ሰዎች ይሞታሉ፡፡ በበሽታ፣ በአደጋ ወይንም በግድያ የሰዎች ሕይወት በየጊዜው ይቀጠፋል፡፡ በተለይም በዚህ ትውልድ ዓለማችን በየጊዜው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን አያጣች ነው፡፡ በእርስ በርስ ግጭትና ጦርነት እንዲሁም የሰዎችን ሕይወት እንደ ቅጠል እያረገፈ ባለው ኮሮና በሽታ እጅግ ብዙ ሰዎች ሞተዋል፡፡ 

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ

ሰብእና

የሰው ልጅ የራሱን ህላዌና ባሕሪዩን ሲመረምር ከግዑዙና ከግሡሡ (ከሚዳሰሰው) ቁስ አካላዊ ክልል የወጣና የተለየ ፍጡር መሆኑን ያስተውላል፡፡ እርግጥ ነው፤ በዓለም ውስጥ ከምድራችን ከሚገኙት በተለመደው አባባል ከአራቱ ባሕርያት የተፈጠረና የእነርሱም ተረጂና ተጠቃሚ ቢሆንም ከእነርሱ የበላይነት ችሎታ ስላለው ተፈጥሮውን እየተቆጣጠረ ለአገልግሎት እንዳዋላቸው እናያለን፡፡ …

መክሊት

በምድራዊ ሕይወታችን ሰዎች የራሳችን መክሊት አለን፤ ይህም የእግዚአብሔር መልካም ስጦታ ነው፡፡ ስጦታዎች ሁሉ ከእግዚአብሔር ናቸውና ፈጣሪያችን ከጊዜ (ዕድሜያችን) ጋር ለእያንዳንዳችን ተሰጥኦ አድሎናል፡፡ ለአንዱ ጥበብ ለሌላው ዕውቀት ይሰጣል፤ አንዱን የዋህ ሌላውን ደግሞ ትሑት ያደርጋል፤ አስተዋይነትን ወይንም ብልሀትንም ያድላለል፤ እንዲሁም አንዱን ባለጠጋ ሲያደርገው ገንዘብ የሌለውን ደግሞ ባለሞያ ያደርገዋል፤ አንዱን የሥዕል ተሰጥኦ ሲያድለው ሌላውን ደግሞ ድምጸ መረዋ ያደርገዋል፤ የእግዚአብሔር ሥራ ድንቅ ነውና፡፡…

የጽጌ ጾም

የጌታችንና የእመቤታችን የስደት ወቅት በወርኃ ግንቦት ነው፤ ነገር ግን ዘመነ ጽጌ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችንን በአበባ፣ ጌታችንን ደግሞ በፍሬ እየመሰሉ ለማመስገንና ለማወደስ በሚያስችል ምሥጢር ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የስደቱ ጊዜ በዘመነ ጽጌ እንዲዘከር አድርገዋል፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለዘለዓለሙ የማይደርቀውን የሕይወት ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስን ያስገኘችልን ንጽሕት የማትጠወልግ አበባ ናትና፡፡ …

‹‹በቸልተኝነት እና በግዴለሽነት ፈጣሪን አትርሱ!›› ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ

ቸልተኝነትና ግዴለሽነት በዚህ ትውልድ ከመንጸባረቁም ባሻገር ሰዎች ፈጣሪን ረስተውና ሃይማታቸውን ትተው እንዲኖሩ አድርጓቸዋል፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎችም የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰሙም ሆነ ምንባባትን ሲያነቡ በግዴለሽነትና ቸል ብሎ በማለፍ ሌሎች ነገሮች ላይ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ ምድራዊ ሕይወታቸው ላይ ብቻ በማተኮር ለጥቅም በመገዛትና ጊዜያዊ ደስታን ለማግኘት ሲሉም መንፈሳዊነትን ንቀው ዓለማዊ ሕይወት እየኖሩ ይገኛሉ፡፡