የእምነት አርበኞች!

ዲያቆን ተስፋዬ ቻይ 

ታኅሣሥ ፲፰፳፻፲ .

 

የፈጠረው ሳለ ለክበር ያበቃው

በጊዜያዊ ደስታ ሰይጣን ቢደልለው

ራሱ ለሠራው ለቆመው ጣኦት

ልቡናው ታውሮ ማስተዋል ተስኖት

ሕዝቡን እያሳተ ከገደል ቢመራ

ትእዛዙ ሲፈጸም ለሥጋው የፈራ

የእምነት አርበኖች ሠለስቱ ሕፃናት

ከፊቱ በመቆም መሰከሩ ለእምነት

በእሳት ሲያስፈራ በሚከስመው ነዶ

ጣኦትን ሊያስመልክ ፈጣሪን አስክዶ

ከላይ ከሰማያት መልአክን አውርዶ

እሳቱ ሲበርድ ሰይጣን በዚህ ሲያፍር

ጽናት ተጋድሏቸው ገሀድ ሲመሰክር

ንጉሡም አመነ በሁሉ ፈጣሪ

ሁሉን በጥበቡ በቸር አሳዳሪ

ጥርጥር ጥላቻ እንደ ሰም ቀለጡ

ደቂቃኑ ለዓለም እምነትን ገለጡ

ጽናት፣ ቆራጥነት፣ እምነት መከባበር

እንደ ወርቅ ነጥረው ታዩ ያኔ በክብር!