የኀዘን መግለጫ
“ብንኖረም ብንሞትም ለእግዚአብሔር ነን”፤ሮሜ ፲፬፥፰
እሁድ መጋቢት ፩ ቀን ፳፻፲፩ ዓ.ም. ከጠዋቱ ፪፡፵፰ ደቂቃ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተነስቶ ወደ ኬንያ ናይሮቢ በመጓዝ ላይ የነበረው ET ፫፻፪ የመንገዶኞች አውሮፕላን ከ፮ ደቂቃ በረራ በኋላ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ከምትገኘው ደብረዘይት ወድቆ መከስከሱ ይታወቃል፡፡በመሆኑም ፻፵፱ መንገደኞች ፰ የበረራ አስተናጋጆችን ጨምሮ በድምሩ ፻፶፯ ሰዎች በሙሉ የአደጋው ሰለባ ሆነዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ፲፯ ያህሉ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ የ፴፫ ሀገራት ዜጎች መሆናቸው ታውቋል፡፡ በዚህ ድንገተኛ ክስተት ለተጎዱ መላው ወገኖቻችን፤ ኢትዮጵያውያንንና ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ዕቅፍ ያሳርፍልን ፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ይሰጥልን ዘንድ እንጸልያለን፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን