የማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን መርሐ ግብር እሁድ ይጀምራል
የካቲት 13 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በማኅበረ ቅዱሳን ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ዋና ክፍል እየተዘጋጀ የሚቀርበው የቴሌቪዥን መርሐ ግብር እሑድ የካቲት 17 ቀን 2005 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 – 4፡00 ሰዓት ድረስ በናይል ሳት ኢቢኤስ ላይስርጭቱን እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ የቴሌቪዥን ስርጭቱ እንደሚጀመር ብንዘግብም በኢቢኤስ የስርጭት መቋረጥ ምክንያት ሳይተላለፍ መቆየቱ ያታወሳል፡፡ በአሁኑ ወቅት በኢቢኤስ ላይ የተከሰቱት ችግሮች የተቀረፉ በመሆናቸው በየሳምንቱ እሁድ ከጠዋቱ 3፡30 – 4፡00 ሰዓት ፤ እንዲሁም በድጋሚ በየሳምንቱ ሐሙስ ከጠዋቱ 1፡00 – 1፡30 ሰዓት የሚተላለፍ መሆኑን የቴሌቪዥን ክፍሉ አስተባባሪ የሆኑት ዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ ገልጸዋል፡፡
በምእመናን በጉጉት ይጠበቅ የነበረው ይህ መርሐ ግብር በተደጋጋሚ በተከሰተው ችግር ምክንያት በመቋረጡ ዝግጅት ክፍሉ ይቅርታ እየጠየቀ ከእሑድ የካቲት 17 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ መከታተል እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡