የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ቅድመ ዝግጅት በኦሎንኮሚ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን
⢠መርሐ ግብሩ በማኅበሩ ድረ ገጽ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ይተላለፋል፡፡
መጋቢት 11 ቀን 2007 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ማኅበረ ቅዱሳን መጋቢት 13 ቀን 2007 ዓ.ም. በምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በደንዲ ወረዳ ቤተ ክህነት ኦሎንኮሚ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የሚካሔደው የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ቅድመ ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ ነው፡፡
አዘጋጅ ኮሚቴው ከቤተ ክርስቲያኑ ሰበካ ጉባኤና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት መርሐ ግብሩን የተሳካ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡ ኮሚቴው ወደ ስፍራው በመጓዝም ክንውኑን ገምግሟል፡፡
ÃÃÂ
የድንኳን ተከላው እየተፋጠነ ሲሆን፤ ጊዜያዊ የመጸዳጃ ቤቶች ዝግጅት ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቁን አረጋግጧል፡፡ የተግባር ቤት፤ የመኪና ማቆሚያ፤ የምግብ መስተንግዶ ስፍራዎች ተለይተዋል፡፡ በምእመናን አቀባበል ሁኔታም ዝግጅቶችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የማኅበሩ ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል በማኅበሩ ድረ ገጽ ላይ የቀጥታ ሥርጭት ለማድረግ ባለሙያዎችን ስፍራው ድረስ በመላክ ማስተላለፍ እንደሚችል ሙከራ አድረጎ ተመልሷል፡፡ በዚህም መሠረት በእለቱ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ መርሐ ግብሩን በቀጥታ ያስተላልፋል፡፡
የኦሎንኮሚ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በ1907 ዓ.ም. የተተከለ ሲሆን፤ 100ኛ ዓመቱን ጥር 16 እና 17 ቀን 2007 ዓ.ም. በድምቀት አክብሯል፡፡ ታቦቱም በ1906 ዓ.ም. ከወሎ ክፍለ ሀገር ወረኢሉ እንደመጣ፤ አሁን ባለበት ቦታ ላይ ከመተከሉ በፊት በኤጄርሳ ለፎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ለአንድ ኣመት በደባልነት ቆይቷል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ የተተከለው በከፍታ ቦታ ላይ በመሆኑ ቀድሞ የአካባቢው ልጆች በየዓመቱ የደብረ ታቦርን በዓል ያከብሩበት ነበር፡፡ ቦታውም âየልጆች ተራራâ እየተባለ ሲጠራ ቆይቷል፡፡