ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም (ክፍል አራት)
በዲ/ን ዮሐንስ ልሳነወርቅ
7. የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም (The interpretation of Scripture)
(ግንቦት 19/2003 ዓ.ም)
ለቅዱስ ኤፍሬም ስለ እግዚአብሔር የሰው ልጅ እውቀት ቀዳሚ ምንጩ በመጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ራሱ ስለ ራሱ እንዲባል የፈቀደውን ነው። የእግዚአብሔር ስሞችና በቅዱስ መጽሐፍ ያሉ የተለያዩ ዓይነቶችና ምሳሌዎች በእግዚአብሔርና በሰውነት መካከል መገናኛ ነጥብን ይፈጥራሉ፤እግዚአብሔር በፈጣሪ ትሕትናው የሰው ልጅ ሊረዳው ወደ ሚችለው ደረጃ ራሱን ዝቅ አደረገ። በሰው ልጅ በኩል በእግዚአብሔር የተሰጠውን ራሱን ወደማወቅ ወደሚወስደው መንገድ የመቅረብ ዕድል ለመጠቀም ከተፈለገ ሁለት ነገሮች አስፈላጊ ናቸው፤በመጀመሪያ ደረጃ ቀድመን እንደተማርነው በመጽሐፍ ቅዱስ ፈጽሞ ለእግዚአብሔር የተጠቀመባቸው ስሞችንና ስእላዊ አገላለጾችን ጥሬ ትርጉም በመውሰድ ያልተገባን ስህተት ልንፈጽም አይገባም፤በሁለተኛ ደረጃም የአንባቢው ዝንባሌ የመቀበልና ቀናነት መሆን አለበት። ቅዱስ መጽሐፍን በተሳሳተ ዝንባሌ ወይም በራሱ ግንዛቤ የሚቀርብ ከሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ምንም ዓይነት እውቀት ለማግኘት ይሳነዋል ብቻ ሳይሆን ወደ ኃጢአትም ሊገባ ይችላል።
ይህ ትምህርታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቅነት ነው፤ያ የትምህርት መስክ ባለፈው ክፍለ ዘመን እንደ ማደጉ ፣ስለዚህ ይህ ታሪካዊ እይታ በጣም ትኩረት የሚሰጥበት ትርጉም ሆኗል።ለቅዱስ ኤፍሬም ግና ይህ እይታ በቂ አይደለም ፤ታሪካዊ እውነታን ብቻ የሚመለከት እንደመሆኑ ፣የእምነት ዓይን ብቻ ከታሪካዊው ሰው ኢየሱስ ወደ ሥግው ክርስቶስ መሄድ እንደሚችል ሁሉ በቅዱስ መጽሐፍም ውሳጣዊ ትርጉሙን ለመመርመር ወደ ውስጥ መዝለቅ የሚችለው የእምነት ዐይን ብቻ ነው።
ቅዱሳት መጻሕፍቱ እንደመስታወት ተቀምጠዋል
ዓይኑ ብሩህ የሆነዉም በዚያ ውስጥ የእውነትን ምስል ያያል።(Faith 67:8)
እንደ መንፈሳዊ ትምህርት አዋቂነቱ ቅዱስ ኤፍሬም በቀዳሚነት አግባብነት ባለው አመለካከትና በዚህ ውሳጣዊው የእምነት ዓይን ብቻ ሊታይ የሚችል ውሳጣዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም መመልከትን ይወዳል ። እንዲያዉም ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ እግዚአብሔር የሚሉትን ውጫዊ ዓረፍተ ነገሮችን ከመመልከት ማቆምና ጥሬ ትርጉማቸውን መውሰድ ሁለቱም እኩል አደገኞች እንደሆኑ በአጽንኦት ይገልጻል፤ ስለ እግዚአብሔር ማንነት ወደ ተሳሳተ አረዳድ ስለሚወስድ፤በተመሳሳይ ጊዜም በአጠቃላይ በትሕትና በሰው ቋንቋ እንዲነገር ለፈቀደ ለራሱ ለእግዚአብሔር የምሥጋና አልባ ንግግር ምልክትና ስለ እግዚአብሔር ትሕትና በአግባቡ አለመረዳት ነው።
አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ኃይል ለመግለጽ በተቀመጡ በስእላዊ አገላለጾች ላይ ብቻ
አትኩሮቱን የሚያደርግ ከሆነ
እግዚአብሔር ለራሱ ለሰው ልጅ ጥቅም ራሱን በሰወረባቸው
በእነዚያ ስእላዊ አገላለጾች አማካይነት
ያንን ኃይል በማይገባ መልኩ ይወክለዋል፤አይረዳዉምም
እንዲሁም ለዚያ ክብር አይገባም
ምንም እንኳ ከእርሱ ጋር የጋራ ነገር ባይኖረውም
ማንነቱን ወደ ሰው ልጅ ደረጃ ያወረደ
ሰውነትን ወደ ራሱ መውደድ ያመጣ ዘንድ
እርሱ ራሱን በሰው ልጅ መውደድ ውስጥ ሰወረ(Paradise 11:6)
ቅዱስ ኤፍሬም በቅዱሳት መጻሕፍት ውጫዊ ትርጉም ላይ ምንም ፍላጎት እንደሌለው ወይም ምንም ጥቅም እንደማይገኝበት አድርጎ እንደሚረዳ ልናስብ አይገባም። ይኽ ውጫዊው ትርጓሜ የክርስቶስ ሰውነት ያህል አገልግሎት አለው።የመጽሐፍ ቅዱስ ውጫዊው ታሪካዊ ትርጉምና ውስጣዊው መንፈሳዊ ትርጉም እጅግ እንደተሳሰሩና እንደ ተያያዙ በሰው ልጅ ውስጥ እንደ ሥጋና ነፍስ፣በክርስቶስ ውስጥም እንደ ሰውነትና ፈጣሪነት ናቸው።ለቅዱስ ኤፍሬም ጠቃሚ የሆነው የእነዚህ ሁሉ ጥንዶችን ግንኙነትና መስተጋብር መረዳት ነው። በየትኛዉም መንገድ ዙሪያ ቢሆንም የአንዱን ጥቅም በመካድ በሌላኛው ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ አደገኛና የተሳሳተ ነው።ስለዚህ ከአይሁድ ጋር የነበረው የቅዱስ ኤፍሬም ጥል ፡አይሁድ እነደ እርሱ አባባል በክርስቶስ ወደ ማመን ይመራቸው የነበረውን ወደ ውስጥ ጠልቀው ማየትን መቃወማቸው፡የኢየሱስ ሰውነትን ብቻ ማየታቸው እንዲሁም የቅዱሳት መጻሕፍት ውጫዊ ትርጓሜ ብቻ ማየታቸው ነው።
አይሁድ ህጉን ማጥናትንና ምክንያት መፈለግን
ባለመቻላቸው አፍረዋል
ይልቁን ከቃላቱ ድምጾች ራሳቸውን ካለ ምንም መረዳት ውስጥ በመዝጋት
የትእዛዛቱን ትርጉም ቀላቀሉ
እውነተኛዉንና ትክክለኛውን
የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጓሜ ሊያዩበት
የሚችሉበትን አስተሳሰብ ለማግኘት
አልደከሙምና (Heresies 50:4)
ቅዱስ ኤፍሬም በውጫዊ ታሪካዊና ውስጣዊ መንፈሳዊ የቅዱሳት መጻሕፍት እይታዎች መካከል መሠረታዊ ልዩነት እንዳለ በውል የተረዳ ነው። የመጀመሪያው(ታሪካዊው) በፍጥረት ክልል ውስጥ ያለው ውሱን ነው፤ትርጓሜዎች ቢያንስ በክልስ ሀሳብ ደረጃ ሊወሰኑና ጠቅላይ ሊሆኑ ይችላሉ። በሌላ በኩል መንፈሳዊ ትርጓሜ በተለዩ ህጎች ውስጥ የሚሠራ ነው፤እንዲሁም በዋናነት ሰፊ ነው፤ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞችም ውሱን አይደሉም። እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ያስቀመጣቸው ስሞች በተፈጥሮና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሁሉም ስፍራ የሚገኙት ምሳሌዎችና ዓይነቶች ለእውነት እንደ መስኮቶች ወይም ትናንሽ ቀዳዳዎች ናቸው። እንዲያዉም በመጀመሪያ ደረጃ በእነዚህ ትናንሽ ቀዳዳዎች ለማየት መሠረታዊው ቅድመ ሁኔታ የእምነት ዓይን ነው፤ አንዴ ከመጀመሪያ መኖሩ ከተረጋገጠ ግና ይኽ የእምነት ዓይን ከተለያዩ ሰዎች ጋር በተለያዩ መንገዶች ይሠራል፤ወይም እንዲያዉም በአንድ ሰው ውስጥ በተለያዩ መንገዶች ግና በተለያዩ ጊዜያት ይሠራል። ውሳጣዊ ዓይኑ የጠፋበት ሰው ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መመልከት አይችልም፤ ውስጣዊ ዐይኑ የሚያበራና ግልጽ የሆነ ግና ትልቅን ጉዳይ ያስተውላል። "ማንኛዉም ሰው ከትህትናው መጠን ጋር በተያያዘ መልኩ ከሁሉም የበለጠውን እርሱን (እግዚአብሔርን) ይረዳል።”(Nativity 4:200)
የእምነት ዓይን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በትኩረት ይመለከት ዘንድ እንዲህ ዓይነቱ የእውነት ወይም መንፈሳዊ እውነታ ትልቅ ሀብት ቢሆንም ማንም ግለ ሰብእ ሁሉንም ነገር የመረዳት ችሎታ የለዉም።ስለዚህም ውሳጣዊው ዓይን ይሆናሉ ብሎ የሚያስተውላቸው ትርጓሜዎች ወሰን የለሽ ናቸው።
ለመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት አንድ ትርጉም ብቻ ቢኖር ኖሮ የመጀመሪያው ተርጓሚ ትርጉሙን ያገኘው ነበር፤ሌሎች አድማጮችም የመፈለግን ድካምና የማግኘትን ደስታ ባልተጋሩ ነበር። ይልቁን እያንዳንዷ የጌታችን ቃል የራሷ መልክ አላት፤እያንዳንዷ መልክም የራሷ አካል አላት፤ እያንዳንዷም አካል የራሷ መለያ አላት።እያንዳንዱም ሰው እንደየዓቅሙ ይረዳል ፤በተሰጠው መጠንም ይተረጉማል። (Commentary on the Diatessaron 7:22)
አንዱ ትርጉም ትክክል ሌላው ስህተት የሚሆንበት አይደለም(ሁልጊዜ በታሪካዊ እይታ ሊሆን እንደሚችለው) ይልቁን ለአንድ ግለሰብ በተወሰነ ጊዜ ትርጉም ያለው እስከሆነ ድረስ የተገባ ትርጓሜ ነው።ስህተት የሚፈጠረው አንድ ሰው የራሱ መንፈሳዊ ትርጓሜ ብቻ ትክክል እንደሆነ ሲናገርና የአንድ ምንባብ ውጫዊና ውስጣዊ ትርጓሜዎች አይገናኙም ብሎ ሲያስብ ብቻ ነው።ይኽ በዋናነት ያ ጉዳይ አይደለም ሁለቱም የትርጓሜ ዓይነቶች ፡ታሪካዊው በአፍአዊው ስሜትና መንፈሳዊው በውሳጣዊው ስሜት በማተኮሩ በሁለት ፈጽሞ በተለያዩ የእውነታ አገላለጽ ወይም እውነታ ዙሪያ ያጠነጥናሉ፤ እንዲሁም አንደኛው እውነታ ሌላኛውን አያጠፋዉም ፤ሁለቱም አገላለጾች በአንድነት ጎን ለጎን በጋራ ሊኖሩ ይችላሉ።
ግልጽ ለሆኑ ምክንያቶች ቅዱስ ኤፍሬም ስለ ታሪካዊ ትርጓሜ የሚያትተው አልፎ አልፎ ብቻ ነው፤በዚህ ደረጃ ሲናገርም እሱ ሊለው የሚገባው እጅግ አርኪ አይደለም፤እጅግ በጣም ውስብስብ በሆኑት፣ባለፈው ዘመን ባደጉት የታሪካዊ ትርጓሜ ስልቶች ሲመዘን። ግን የእርሱ ዋና ጉዳይ ውስጣዊ፣መንፈሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በሆነበት ቦታ ሁሉ(ይኽም የእርሱ የሁል ጊዜ ጉዳይ ነው) በዚያ የእርሱ ምልከታዎች አሁንም ቢሆን ጥልቅ እይታ ያላቸው በመሆኑ አስተዋይ ዘመናዊ አንባቢዎችን መማረክ ይችላሉ።
በዚህ ክፍል የቅዱስ ኤፍሬም መጽሐፍ ቅዱስን የመረዳት ምንነትና ትርጉም የመሰለኝን እየለየሁ ነው፤እንዲሁም እርሱ ራሱ በቀጥታ እንዲናገር ሊፈቀድለት አሁን ጊዜው ነው።
በዚህ ምንባብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥቅዱስ ኤፍሬም ስለ ውሳጣዊ ትርጓሜዎች መብዛት ለክርስቶስ በመናገር ይጀምራል።
በአንተ(እግዚአብሔር) አንድ አባባል ውስጥ የሚፈለገውን ስፋት ሁሉ መረዳት የሚችል ማን ነው? ከእርሱ ከምንወስደው በራቀ መልኩ ከእርሱ ብዙ እንተዋለንና ፤የተጠሙ ሰዎች ከምንጭ እንደሚጠጡት ። የእርሱ (እግዚአብሔር) እይታዎች ከእርሱ ከሚማሩት እይታዎች እጅግ የበዙ ናቸውና።እግዚአብሔር እያንዳንዱ ከቃሉ የሚማር እርሱ የፈለገውን አቅጣጫ እንዲያይ በሚያስችል መልኩ ቃሉን በብዙ ውበቶች ገልጾአል።እንዲሁም እግዚአብሔር እያንዳንዳችን በእርሱ በየትኛዉም አቅጣጫ ላይ በመመሰጥ ባዕለጸጋ እንሆን ዘንድ በቃሉ ውስጥ ሁሉንንም የስጦታ ዓይነቶችን ሰውሮአል።የእግዚአብሔር ቃል የሕይወት ዛፍ ነውና በሁሉም አቅጣጫ ላንተ የተባረኩ ፍሬዎችን የሚሰጥ ፤እርሱ በምድረ በዳ እንደተሰነጠቀው ዐለት ነው ፤በሁሉም አቅጣጫ ለእያንዳንዱ መንፈሳዊ መጠጥ የሆነው።እነርሱ የመንፈስን መብል በሉ፤የመንፈስንም መጠጥ ጠጡ።
ማንኛዉም መጽሐፍ ቅዱስን የሚመለከት ሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ሀብቶች ሁሉ ያገኘውን አንዱን ብቸኛ ያለ አድርጎ ሊወስድ አይገባውም፤ይልቁንም እርሱ ራሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉት ከብዙ ሀብቶች መካከል ያገኘውን አንዱን ብቻ መፈለግ እንደቻለ ሊያስተውል ይገባል።
እንዲሁም አንባቢው እርሱን ሀብታም ስላደረገው መጽሐፍ ቅዱስ ምሥጢር ያለቀበት ደሀ አድርጎ ሊያስብ አይገባም።ይልቁንም አንባቢው ተጨማሪዎችን ማግኘት ካልቻለ የመጽሐፍ ቅዱስን ጥልቀት ያመሥግን።እርካታ ስላገኘህ ተደሰት ፤የሆነ ነገር ስለቀረብህ አትዘን።የተጠማ ሰው ስለጠጣ ያመሠግናል፤ምንጩን በመጠጣት ሊያደርቀው አለመቻሉን በማረጋገጡ አያዝንም።ምንጩ ያንተን ጥማት ይቁረጥ ያንተ ጥማት ምንጩን አያድርቅ!ምንጩ ሳይቀንስ ጥማትህ ቢቆረጥ በተጠማህ ጊዜ እንደገና ትጠጣለህ፤ነገር ግን አንዴ ከረካህ በኋላ ምንጩ ደርቆ ቢሆን ኖሮ በምንጩ ላይ ያገኘኸው ድል ያንተን ጉዳት ባረጋገጠ ነበር።ስለወሰድከው ምስጋናን ስጥ እንዲሁም በዝቶ ስለተረፈው አታጉረምርም።አንተ ለራስህ የወሰድከው የራስህ ድርሻ ነው፤የተረፈው አሁንም ያንተ ውርስ ሊሆን ይችላል።( Commentary on the Diatessaron 1:18-19)
ይቆየን