ሰዋሰወ ግእዝ ክፍል አራት
ሐምሌ 3 ቀን 2005 ዓ.ም.
በመ/ት ኑኀሚን ዋቅጅራ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
- ፊደል ብሂል – ርዕሰ መጻሕፍት -የመጻሕፍት (የጽሑፍ) መጀመሪያ
- ፊደል ብሂል – ነቅዓ ጥበብ – የጥበብ ምንጭ /የእውቀት መፍለቂያ/
- ፊደል ብሂል – መጽሔተ አእምሮ – የአእምሮ መስታወት
- ፊደል ብሂል – ጸያሔ ፍኖት – መንገድ ጠራጊ /በር ከፋች/
- ፊደል ብሂል – መራሔ እውራን ውእቱ – ፊደል ሰዎችን ካለአዋቂነት /ከድንቁርና እውርነት አውጠቶ ወደ ብርሃን የሚመራ ነው፡፡
ባለፈው ሳምንት አምዳችን ስለ ግእዝ ፊደላትና ስለ ዝርዋን የግእዝ ፊደላት የአዘራዘር ሥልትና የፊደላት ትርጉም ተመልክተናል፡፡ በዛሬው አምዳችን ደግሞ ስለ አማርኛ ፊደላትና የአማርኛ ዝርዋን ፊደላትን እንመለከታለን፡፡
የአማርኛ ፊደላት የምንላቸው በቁጥር ፯/ሰባት/ ናቸው፡፡ የአማርኛ ፊደላት ከጊዜ በኋላ በዋንኞቹ የግእዝ ፊደላት ላይ የተወሰነ ቅጥያ በማድረግ የተመሠረቱ ፊደላት ናቸው፡፡ የአማርኛ ፊደላት የአዘራዘር ሥልት እንደ መነሻዎቹ የግእዝ ፊደላት ሲሆን በግእዝ በካዕብ በሣልስ በራብዕ በኀምስ፣ በሳድስና በሳብዕ የአዘራዘር ሥልት ይዘረዘራሉ፡፡ የአማርኛ ፊደላት የአማርኛ ፊደል የተባሉበት ዋናው ምክንያት በግእዝ ቋንቋ በሚዘረዘሩ ግሦችና የፊደላት ትርጉም አለመጠቀሳቸውና አብዛኛውን ጊዜ በግእዝ ቋንቋ በሚጻፉ ጽሑፎችና ሥነ ጽሑፍ ላይ አለመጠቀሳቸውም ነው፡፡ ለአማርኛ ፊደላት መነሻ የሆኑትን የግእዝ ፊደላትና የአማርኛ ፊደላትን ከነአዘራዘራቸው በቅደም ተከተል ከዚህ በመቀጠል እንመለከታለን፡፡
ከዚህ የምንረዳው በፊደል ገበታ ላይ የአማርኛ ፊደላት ተብለው ከሚጠሩት ፊደላት መካከል እነዚህ ፯/ሰባት/ ፊደላት ብቻ ሌሎቹ የግእዝ ፊደላት መሆናቸው ነው፡፡
መነሻ የግእዝ ፊደላት |
ግእዝ |
ካዕብ |
ሣልስ |
ራብዕ |
ኀምስ |
ሳድስ |
ሳብዕ |
፩ ሰ |
ሸ |
|
|
|
|
|
|
፪ ተ |
ቸ |
|
|
|
|
|
|
፫ ነ |
ኘ |
|
|
|
|
|
|
፬ ከ |
ኸ |
|
|
|
|
|
|
፭ ዘ |
ዠ |
|
|
|
|
|
|
፮ ደ |
ጀ |
|
|
|
|
|
|
፯ ጠ |
ጨ |
|
|
|
|
|
|
ከዚህ በመቀጠል ደግሞ የአማርኛ ፊደል ዲያሎችን /ዝርዋን የአማርኛ/ ፊደላትን እንመለከታለን፡፡
ዝርዋን የአማርኛ ፊደላት
ዝርዋን ማለት ብትን ሕግንና ቅደም ተከተልን ያልጠበቀ ማለት ነው፡፡ ዝርዋን የአማርኛ ፊደላት የምንላቸው በግእዝና በአማርኛ ፊደላት ላይ በተለየ መልኩ በራብዑ /በአራተኛው/ ፊደል ዝርዝር ላይ በስተመጨረሻ ወይም ከላይ ቅጥያ በማድረግ የተፈጠረ ፊደልና በአንድ ነጠላ ዝርዝር ብቻ የሚገለጽ በአማርኛ ጽሑፍ ላይ ብቻ የሚገኝ የፊደል ዝርዝር ነው፡፡ ዝርዋን የአማርኛ ፊደላት አብዛኛውን ጊዜ የሚያገለግሉት በአንስታይ /በሴት/ ጾታ ማለትም በሩቅ ድርጊት አመልካች በነጠላ የሴት ጾተ የሚገለጸውን ቃል የእራስነትዋን ለመግለጽ የምንጠቀምበትን ቃል ሁለት ተከታታይ ሳድስና ራብዕ ፊደላትን በመዋጥ በአንድ ፊደል በዝርው የአማርኛ ፊደል በመተካት የፊደላትን ቁጥር በመቀነስ ያገለግላል፡፡
ዝርዋን የአማርኛ ፊደላት የሚባሉት
ሏ፣ ሟ፣ ሿ፣ ሯ፣ ቧ፣ ቷ፣ ዟ፣ ዧ፣……. ናቸው፡፡
ምሳሌ፡- ልብዋ …. ልቧ፣ ቤተሰብዋ…..ቤተሰቧ
እርስዋ… እርሷ፣ እጅዋ….. እጇ ወዘተ…….
ለዛሬ ያለንን አምድ በዚህ እናበቃለን በቀጣይ ሳምንት የግእዝ አኀዝ ቁጥሮችን የአጻጻፍና የአነባበብ ሥልት እንመለከታለን እስከዚያው ቸር ይግጠመን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር