ሥረይ ግሦች

ክፍል ሦስት

ኅዳር ፳፮ ቀን ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት

የተወደዳችሁ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? የእግዚአብሔር አምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን! የዚህን ዓመት የኅዳር የመጨረሻ ክፍለ ጊዜያችን የሆነውን ትምህርት ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ ከባለፈው ትምህርታችን ቀጣይ ወይም ሦስተኛና የመጨረሻ የሆነውን ትምህርታችንን ከማቅረባችን በፊት በ ‹‹ሥረይ ግሥ›› ክፍል ሁለት ትምህርታችን ለማየት የሞከርነው  በግእዝ ቋንቋ ከግሥ ዓይነቶች አንዱ የሆነው ሥረይ ግሥን በግሥ አርእስት በቀተለ፣ በቀደሰ፣ በተንበለ፣ በባረከና በማህረከ ሥር መድበን ርባታቸውን እንደሆነ እያስታወስናችሁ በመቀጠል ደግሞ በዴገነ/ሴሰየ፣ በክህለ እና በጦመረ ሥር የሚመደቡ ሥረይ ግሦችን እናቀርብላችኋለን፡፡

. በዴገነ/ሴሰየ ሥር የሚመደቡ ሥረይ ግሦች

አቅዜዘየ ቅዝዝ አለ ኃላፊ አንቀጽ
ያቅዜዚ ቅዝዝ ይላል ትንቢት አንቀጽ
ያቅዜዚ ቅዝዝ ይል ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ያቅዜዚ ቅዝዝ ይበል ትእዛዝ አንቀጽ
አቅዜዝዮ/አቅዜዝዮት ቅዝዝ ማለት ንዑስ አንቀጽ
አቅዜዛዪ ቅዝዝ የሚል ሣልስ ቅጽል
አቅዜዛዪት ቅዝዝ የምትል አንስታይ ቅጽል
አቅዜዝዮ ቅዝዝ ብሎ ቦዝ አንቀጽ
አንጌገየ ተቅበዘበዘ ኃላፊ አንቀጽ
ያንጌጊ ይቅበዘበዛል ትንቢት አንቀጽ
ያንጌጊ ይቅበዘበዝ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ያንጌጊ ይቅበዝበዝ ትእዛዝ አንቀጽ
አንጌግዮ/አንጌግዮት መቅበዝበዝ ንዑስ አንቀጽ
አንጌጋዪ የሚቅበዘበዝ ሣልስ ቅጽል
አንጌጋይት የምትቅበዘበዝ አንስታይ ቅጽል
እንጊጉይ የተቅበዘበዘ ሳድስ ቅጽል
እንጊጉይት የተቅበዘበዘች አንስታይ ቅጽል
አንጌግዮ ተቅበዝብዞ ቦዝ አንቀጽ
አንጌግያ ተቅበዝብዛ ቦዝ አንቀጽ

ከዚህ በታች ያሉት ሥረይ ግሦች የሚለዩ ትንቢት ዘንድ እና ትእዛዝ አንቀጽ በቅርጽ አንድ ሆነው በመጥበቅና በመላላት ነው። የትንቢታቸው መድረሻ ድምጽ ይጠብቃል ዘንድ እና ትእዛዛቸው ይላላል።

ዜነወ ነገረ፣ አወራ ኃላፊ አንቀጽ
ይዜኑ ያወራል ትንቢት አንቀጽ
ይዜኑ ያወራ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይዜኑ ያውራ ትእዛዝ አንቀጽ
ዜንዎ/ዜንዎት ማውራት ንዑስ አንቀጽ
ዜናዊ ነጋሪ ወሬኛ ሣልስ ቅጽል
ዜናዊት የምታወራ አንስታይ ቅጽል
መዜንው የሚያወራ ባዕድ አንስታይ ቅጽል
መዜንውት የምታወራ ባዕድ ቅጽል
ዜና ወሬ ዘመድ ዘር
ዜንዎ አውርቶ ቦዝ አንቀጽ
ጌገየ በደለ፣ ሳተ ኃላፊ አንቀጽ
ይጌጊ ይበድላል ትንቢት አንቀጽ
ይጌጊ ይበድል ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይጌጊ ይበድል ትእዛዝ አንቀጽ
ጌግዮ/ጌግዮት መበደል ንዑስ አንቀጽ
ጌጋዪ በዳይ/የሚበድል ሣልስ ቅጽል
ጊጉይ የተበደለ  ሳድስ አንስታይ ቅጽል
ጊግይት የተበደለች አንስታይ ቅጽል
ጌጋይ ስሕተት፣ በደል ዘመድ ዘር
ጌግዮ በድሎ ቦዝ አንቀጽ

. በክህለ ሥር የሚመደቡ ሥረይ ግሦች

ስሕወ ተሳበ፣ ተጐተተ ኃላፊ አንቀጽ
ይስሑ ይስባል ትንቢት  አንቀጽ
ይስሐው ይሳብ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይስሐው ይሳብ ትእዛዝ አንቀጽ
ስሒው/ስሒዎት መሳብ ንዑስ አንቀጽ
ሰሐዊ የሚሳብ ሣልስ ቅጽል
ሰሐዊት የምትሳብ አንስታይ ቅጽል
ስሕው ተስቦ ዘመድ ዘር
ስሒዎ ተስቦ፣ ተጎትቶ ቦዝ አንቀጽ
ጥዕየ ዳነ፣ ተፈወሰ ኃላፊ አንቀጽ
ይጥዒ ይድናል ትንቢት አንቀጽ
ይጥዓይ ይድን ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይጥዓይ ይዳን ትእዛዝ አንቀጽ
ጥዕይ/ጥዕዮት መዳን ንዑስ አንቀጽ
ጥዑይ የዳነ ሳድስ ቅጽል
ጥዕይት የዳነች ሳድስ አንስታይ ቅጽል
ጥዒና ጤና፣ደኅንነት ዘመድ ዘር
ጥዒዮ ድኖ ቦዝ አንቀጽ
ጥዒያ ድኖ ቦዝ አንቀጽ

. በጦመረ ሥር የተመደቡ ሥረይ ግሦች

ሎለወ ጠበሰ፣ለበለበ ኃላፊ አንቀጽ
ይሎሉ ይጠብሳል ትንቢት አንቀጽ
ይሎሉ ይጠብስ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይሎሉ ይጥበስ ትእዛዝ አንቀጽ
ሎልዎ/ሎልዎት መጥበስ ንዑስ አንቀጽ
ሎላዊ የሚጠብስ፣ጠባሽ ሣልስ ቅጽል
ሎላዊት የምትጠብስ አንስታይ ቅጽል
ሎሊዎ ጠብሶ ቦዝ አንቀጽ
ሞርቅሐ ላጠ ኃላፊ አንቀጽ
ይሞረቅሕ ይልጣል ትንቢት አንቀጽ
ይሞርቅሕ ይልጥ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይሞርቅሕ ይላጥ ትእዛዝ አንቀጽ
ሞርቅሖ/ሞርቅሖት መላጥ ንዑስ አንቀጽ
ሞርቃሒ የሚልጥ ሣልስ ቅጽል
ሞርቃሒት የምትልጥ አንስታይ ቅጽል
አልኆሰሰ ሹክ አለ ኃላፊ አንቀጽ
ያልኆስስ ሹክ ይላል ትንቢት አንቀጽ
ያልኆስስ ሹክ ይል ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ያልኆስስ ሹክ ይበል ትእዛዝ አንቀጽ
አልኆስሶ/አልኆስሶት ሹክ ማለት ንዑስ አንቀጽ
አልኆሳሲ አሾክሹዋኪ ሣልስ ቅጽል
አልኆሳሲት ሹክ የምትል አንስታይ ቅጽል
ለኆሳስ ቀስታ፣ ሹክሹክታ ዘመድ ዘር
አልኆሲሶ ሹክ ብሎ ቦዝ አንቀጽ
አልኆሲሳ ሹክ ብላ ቦዝ አንቀጽ
አክሞሰሰ ፈገገ፣ ፈገግ አለ ኃላፊ አንቀጽ
ያክሞስስ ይፈጋል ትንቢት አንቀጽ
ያክሞስስ ይፈግ ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ያክሞስስ ይፍገግ ትእዛዝ አንቀጽ
አክሞስሶ/አክሞስሶት መፍገግ ንዑስ አንቀጽ
አክሞሳሲ የሚፈግ ሳድስ ቅጽል
አክሞሳሲት የምትፈግ አንስታይ ቅጽል
አክሞሲሶ ፈገግ ብሎ ቦዝ አንቀጽ
ጎርየመ አገመ፣ አከመ ኃላፊ አንቀጽ
ይጎርይም ያግማል ትንቢት አንቀጽ
ይጎርይም ያግም ዘንድ ዘንድ አንቀጽ
ይጎርይም ይገም ትእዛዝ አንቀጽ
ጎርይሞ/ጎርይሞት ማገም ንዑስ አንቀጽ
ጎሬም ዋገምት ዘመድ ዘር
ጎርዩሞ አግሞ ቦዝ አንቀጽ
ጎርዩማ አግማ ቦዝ አንቀጽ

ይቆየን!

ምንጭ፡- ሰዋስው ወልሳነ ግእዝ መጽሐፍ ከገጽ ፻፲፬-፻፲፰