የማኅበረ ቅዱሳን የልኀቀት ማእከል ግንባታ
በዕውቀት ዋጋ
መጋቢት ፪፤፳፻፲፯ ዓመተ ምሕረት
ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ የመተዳደሪያ ደንቡ ጸድቆ ከተሰጠው ጀምሮ አገልግሎቱን የተሻለ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ ማኅበሩ ርእይዩን ከግብ ለማድረስ በሀገር ውስጥና በልዩ ልዩ የውጭ ሀገራት የአገልግሎት መዋቅርን ዘርግቶ ተተኪ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን በማፍራት፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ወጣቶች በሥነ ምግባር እንዲታነጹ በማድረግ ሀገርና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በዕውቀታቸው፣ በገንዘባቸውና በሙያቸው የሚያገለግሉ ሀገር ተረካቢ ትውልድ እያፈራ ይገኛል። ይህንን መጠነ ሰፊ አገልግሎት ለማሳለጥና በሚፈለገው ልክ አገልግሎቱን ለማስሄድ ሁለተኛ ዙር ጽሕፈት ቤት መገንባት ግድ ሆኖበታል። ማኅበሩ እየተጠቀመበት ያለው ሕንጻ ዕለት ዕለት እያደገ ከመጣው የማኅበሩ የአገልግሎት መስፋት አንጻር ሲነጻጸር ተመጣጣኝ ባለመሆኑ በአሁኑ ሰዓት የሁለተኛ ዙር ጽሕፈት ቤት ግንባታ በይፋ ጀምሯል።
የልኅቀት ማእከሉ 500 ካሬ ላይ ያረፈ ቁመቱ 47 ሜትር፣ ከመሬት በታች 2 ወለል፣ ከመሬት በላይ 14 ወለል ያለው ነው። 61 የመኪና ማቆሚያ፣ ከ960 እስከ 1000 ሰው መያዝ የሚችል ሁለገብ የአገልግሎት አዳራሽ፣ ከ30 እስከ 40 ሰው የሚይዙ የስብሰባና የሥልጠና አዳራሾች፣ ዘመናዊ የብሮድ ካስት አገልግሎት የሚሰጥ ስቱዲዮ እና እንዲሁም ለማኅበሩ መደበኛ አገልግሎት የሚውሉ ደረጃቸውን የጠበቁና ዘመናዊ የሆኑ ቢሮዎች አሉት፡፡
የልኅቀት ማእከሉን ግንባታ ለማጠናቀቅ አሁን ባለው የገበያ ዋጋ 400 ሚሊዮን ብር ይፈጃል። አሁን ላይ ወደታች ሁለት ምድር ቤት ወደ ላይ ደግሞ አራተኛ ወለሉን እየሠራን እንገኛለን።ይህንን ግዙፍ የልኅቀት ማእከል ግንባታ ለማጠናቀቅ የገቢ አሰባሰብ ኮሚቴው ከማኅበሩ ጽሕፈት ቤት ጋር በመቀናጀት መጠነ ሰፊ ሥራዎችን እየሠራ ነው፡፡ ሌሎች የማኅበሩ ባለድርሻ አካላትም ለግንባታው መጠናቀቅ የተሰጣቸውንና የሚሰጣቸውን ኃላፊነት እየተወጡ ይገኛሉ። ስለሆነም ትውልድ የሚታነጽበትን ይህን ግዙፍ የልኅቀት ማእከል ግንባታ ለማከናወን የሁሉንም የማኅበሩ አባላትንና የኦርቶዶክሳዊያንን ተሳትፎ የሚፈልግ በመሆኑ አሻራችሁን እንድታስቀምጡ መልእክታችንን ማስተላለፍ እንፈልጋለን። የዋናው ማእከል የልኅቀት ማእከል ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ የባንክ ሒሳብ ቁጥሮች ከዚህ በታች የተጠቀሱት ናቸው።
1. ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000003780717
2. አሐዱ ባንክ የቁጠባ ሒሳብ ቅድስት ማርያም ቅርንጫፍ አካውንት 0003488710901
3. አቢሲኒያ ባንክ ቅድስት ማርያም ቅርንጫፍ አካውንት ቁጥር 4753388
4. አዋሽ ባንክ አራት ኪሎ ቅርንጫፍ አካውንት ቁጥር 01320021428400
5. ወጋገን ባንክ ቅድስት ማርያም ቅርንጫፍ አካውንት ቁጥር 0057130830101
አምላከ ቅዱሳን ፍጻሜውን ያሳየን!
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!