ድንቅ ነው ማዳንሽ!

ነፍሱ እጅግ ተጨንቃ ሲቃ እያነቃት

የበርባኖስ ጥላ ከላይ ረቦባት

በመልአከ ፅልመት የፊጥኝ ተይዛ

በእሳት ሰንሰለት ሰሌን ተገንዛ

ሰባ ስምንት ነፍሳት ከምድር አጥፍታ

የደም ብድራቷን በአኩፋዳ ሞልታ

ፍርድን ልትቀበል ስትቀርብ ከጌታ

ስለ ድንግል ማርያም ዳነች ከመከራ

የጠቆረች ነፍሱም በምልጇ በራ

በድውይ መዳፍ ላይ በስሟ ያረፈች

ያች ጥርኝ ውኃ ሚዛኑንም ደፋች