[smartslider3 slider="3"]

‹‹ነገን ዛሬ እንሥራ!››

ውድ አንባብያን! የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ስለ ቤተ ክርስቲያን ምንነት፣ ታሪክ ወዘተ መተንተን አይደለም፡፡ የነገዋ ቤተ ክርስቲያን ምን መምሰል አለባት? እንዴትስ ለትውልዱ እስከ ክብሯና ግርማ ሞገሷ ትሻገር? የሚለውን አሳሳቢ ጉዳዮችን መዳሰስ ነው እንጂ፡፡

“ጾማችን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው የተፈናቀሉት ወገኖቻችን ወደ ቀያቸው ተመልሰው ሰላማዊ ኑሮ መኖር ሲችሉ፣ የተራቡት ሲደገፉ፣ ፍትሕ ያጡት ፍትሕ ሲያገኙ ነው፡፡”

አድዋን ያለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማሰብ ትርጉም አልባ ነው!

የቤተ ክርስቲያናችን አስተዋጽኦ የሚገለጠው “እንዴት አሸነፍን?” የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ስንመረምር ነው፡፡ ይህ ዓለምን በብርቱ ጠፍንጎ የያዘና አንዱን ባሪያ ሌላውን ጌታ የሚያደርግ፣ ሰውን ያህል ፍጡር እንደ ከብት ነድቶ፣ እንደ ዕቃ ጎልቶ፣ ለገበያ አቅርቦ የሚሸጥ እኩይ አስተሳሰብ ከመሠረቱ የናደ፣ ነጻነት ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ ለሌሎች ያሳየ፣ የአስተሳሰቡ ሰለባ የነበሩ ነጮችንም ያስደነገጠ ድል ኢትዮጵያውያን እንዴት ሊቀዳጁ ቻሉ? ዓቅሙና ብርታቱስ ከየት ተገኘ? ምዕራባውያን ያላቸው የሠለጠነ ወታደር፣ የጦር መሣሪያ ልዩነት እና ዓለምን የተቆጣጠረው “የነጮች” የበላይነት አስተሳሰብ እያለ የመግጠምስ ሞራሉና እምነቱ ከወዴት መጣ? ኢትዮጵያውያንን ከዚህ የአስተሳሰብና የሞራል ከፍታ ያደረሳቸው ገፊ ምክንያትስ ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን ስንጠይቅ መልሱ ቤተ ክርስቲያናችን ዘንድ ያደርሰናል፡፡