[smartslider3 slider="3"]

ዜና ዕረፍት

የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አበምኔት ታላቁ የጸሎት አባት የኔታ መምህር ሐረገ ወይን ምሕረቱ በእርግና ምክንያት በ፺፱ ዓመታቸው መጋቢት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል።ሥርዓተ ቀብራቸውም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ተፈጽሟል።

የኔታ ሐረገ ወይን በርካታ ጳጳሳትንና ሊቃውንትን አስተምረው ያበቁ የአቋቋሙ ሊቅ ነበሩ። ከአርባ ዓመት በላይ ወንበር ዘርግተው ያስተማሩ፣ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጊዜ ጀምሮ ሁለት ጊዜ ያክል ለጵጵስና ቢጠየቁም “ምንኩስናዬ ይበቃኛል” በማለት በዓታቸውን ያጸኑ ጸሎተኛ አባት እንደነበሩም ተገልጿል።

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፲ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ ድምቀት ተከበረ።