እውነተኛ ፍቅር

ፍቅሩ ስቦህ የአዳም

ልትከፍልለት ዕዳውንም

ከሰማይ ወርደህ…

በጲላጦስ ፊት ስትቀርብ ታስረህ

እንደ ወንበዴም ተቆጥረህ

በዕፀ መስቀል ተሰቅለህ

ሰውን ስትል መከራ አየህ

በቀራንዮም እጅግ ተሰቃየህ

በመስቀሉ ታየ ያንተ ፍቅር

ታምነሀልና እስከ በመቃብር

መኖሬ ሆኖ የአንተ ሕይወት

ስጓዝ በመንገድህ ሆነኸኝ ተምሳሌት

ካንተም አገኘሁ እውነተኛ ፍቅር

ተስፋ የሚሆነኝ ስኖር በምድር