ቸሩ እረኛዬ

ጥቅምት ፳፮ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም

ሰላምን ስሻ በአንተ አምኜ
በጭንቅ በነበርኩበት እጅጉን አዝኜ
በዚህች በከንቱ ዓለም በጨለማ ሆኜ
ፈጥነህ ደረስክልኝ ሆነኸኝ አጽናኜ

ስጓዝ በመንገድህ ካንተ ጋር እኖር ብዬ
ምርኩዜ ሆንከኝ ጥላ ከለላዬ
ከፊቴ መርተኅ ቸሩ እረኛዬ
የልቤን መሻት ፈጸምክልኝ ፈጣሪዬ

ጥበቃህ አይለየኝ ነህና ረዳቴ
ውስጤንም አድሰው ምራኝ በሕይወቴ
ደስታን አየሁብህ ሀብቴና ርስቴ
ዘለዓለም ላመስግንህ በሙሉ አንደበቴ