ፈጣሪዬ እግዚአብሔር

በሕይወት ሳልለው

ፈጥሮኝ በአምሳሉ ከአፈር

አሳድጎኝ በሰላምና በፍቅር

ኑሪ አለኝ ከአምላክሽ ጋር

የጥበብ መገኛ እግዚአብሔር

አስረዳኝ የሥላሴን ምሥጢር

የድንግል ማርያምንም ክብር

በውጣ ውረድ ስኖር በዚህ በምድር

መንገላታቴ በዝቶ ላለመውደቅ ስጥር

ለበጎ ነው ሲል ነገረኝ በፈተና መኖር

ደግሞም አበረታኝ በተግሣፅ በምክር

እንድጸልይ እና  እንድማጸን ዘወትር

ሳልታክትም እንድሰራ ጥሩ ምግባር

አስተማረኝ በቤተክርስቲያን መዘከር

ማመስገንንም ከመላእክት መንደር

በፊቱ ስቀርብ አብሬ እንድከብር

ነይ ብሎ ጠራኝ ከንጹሓን ሰፈር

ብርሃን ከሆነው ከቅዱሳን ሀገር

ነውና ፈጣሪዬ ስመጥር