ቀራንዮ

በመዝሙርና ሥነ ጥበባት ክፍል

ሚያዚያ ፳ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም

ቀራንዮ … ቀራንዮ …ቀራንዮ ጎልጎታ

የተለየሽው ከሁሉ ቦታ

የመከራ ቤት የደም ማማ

የመስቀል ዙፋን የግፍ አውድማ

የሐዲስ ኪዳን አማናዊ መሥዋዕት

የቀረበብሽ ለአዳም ድኅነት

አንቺ…ቀራንዮ ጎልጎታ

መስቀል ተሸከምሽ ለሕይወት ጌታ

አላየሽም…!

የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ሲተረተር

ሙታን ሲነሡ ሲከፈት መቃብር

ጨረቃ በደም ስትለወስ

ፀሐይ ጽልመትን ስትለብስ

ምድር ስትጨልም ሲረግፉ ከዋክብት

ዕፁብ ድንቅ ሲሉ ሊቃነ መላእክት

ቀራንዮ … ቀራንዮ …ቀራንዮ ጎልጎታ

አንችን ምን አጸናሽ ጉልበትሽ በረታ