ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን መግቢያ

በሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ
 
እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሁሉ በሀብት ስቦ በረድኤት አቅርቦ ወደ ራሱ ይጠራቸዋል ፤ ያቀርባቸዋል፡፡ የተጠሩት ደግሞ በንዑሰ ክርስቲያንነት ደረጃ ቃለ እግዚአብሔርን እየሰሙ ከቆዩ በኋላ አዲስ ሕይወትን እንዲቀዳጁና ጸጋ መንፈስ ቅዱስን እንዲያገኙ የሚያበቃቸው ሌላ መንገድና ሥርዓት አስፈላጊ ስለሆነ ጌታ ራሱ አዘጋጅቶላቸዋል ፤ ሁላችንንም በዚህ መንገድ እንድንሄድ አዞናል፡፡ መንገድ የተባለውም ቃሉን ሰምቶ መፈጸምና ያዘዘንን የቤተ ክርስቲያን ምሥጢራት ሁሉ መፈጸም ነው፡፡