መስቀል

በሕይወት ሳልለው

መስቀል የፍቅር ተምሳሌት

የዓለም ሰላምና አንድነት

ጠላት በቀራንዮ የተሸነፈበት

የሰው ልጅ ድኅነት

መስቀል

ብርሃንና ገጸ ምሕረት

ጌታችን ኢየሱስ የተሰቀለበት

የሰው ዳግም ሕይወት

የአዳም ዘር በሙሉ የዳነበት

መስቀል

ማንነታችን የተገለጸበት

የነፍስና የሥጋ በረከት

እውነተኛ ሕይወት

ተዋሕዶ ሃይማኖት

መስቀል