መስቀሉን ይሸከም

ሊሄድ በ’ኔ መንገድ

ሊከተል የሚወድ

ራሱን ይካድ

መስቀሉን ይሸከም

ቢያገኘው መከራም

አይደንግጥ አይፍራ

አለሁ ከ’ሱ ጋራ

ብሎኝ

ትናንትና፡-

ቃሉንም ሰምቼው

አምኜ በነበር

በመከራ እንድከብር

ዛሬ፡-

ፍርሃት ባልተሰማኝ

ሲለኝ

“እኔ ከአንተ ጋር ነኝ!”