የተከናወኑ ዐበይት ተግባራት

ከ፲፱፻፺፭፳፻.

  • ሱቅከፍተው የተለያዩ ገቢ የሚያስገኙ የልማት ሥራዎችን ያከናውኑ ነበር
  • ከአባላትወርኃዊ አስተዋጽኦ እየተሰበሰበ 40% ወደ ዋናው ማእከል ይልኩ ነበር
  • የተወሰኑአባላት ምእመናንን በማስተምሩ ይሳተፉ ነበር

፳፻፩ – ፳፻፫ .

  • ፕሪቶሪያ ያሉ አባላት በዐርብ ጸሎትና በማክሰኞ ጉባኤን ላይ በመካፈል የፕሪቶሪያ ሐመረ ኖኅ ቅ/ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያንን የመደገፍ ሥራ ይሠሩ ነበር
  • ደቡብአፍሪካውያን ካህናት ኢትዮጵያ ሒደው ሥልጠና እንዲያገኙ አግዘዋል
  • ለጉባኤያትመምህራንን በመላክ ስብከተ ወንጌል እንዲስፋፋ አስተዋጽኦ አድርገዋል

በ፳፻፭ ዓ.ም. የተከናወኑ ዐበይት ተግባራት

  • በወቅቱ ብዙ አባላትም ወደ ግ/ጣቢያው የመጡበት ጊዜ ነበር
  • ተቀዛቅዞ የነበረውን በጆሐንስበርግ አገልግሎት ለማጠናከር ውይይት ተደርጓል
  • የሥራ አስፈጻሚ አባላት ምርጫ ተካሂዷል፤ በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ አባላት ሥራ አስፈጻሚ ውስጥ እንዲካታቱ ተደርጓል
  • የሥራ አስፈጻሚ አባላት (ሰብሳቢ፣ ም/ሰብሳቢ፣ ጸሓፊ፣ ግንኙነት፣ ልማት፣ ትምህርት፣ ሒሳብ እና ኦዲትና ኢንስፔክሽን ክፍላት) ተመርጠዋል
  • ክፍሎች በየሁለት ሳምንቱ በስካይፕ ስብሰባ ያደርጉ ነበር
  • የግ/ጣቢያውን የአገልግሎት ለማጠናከርና ተደራሽነቱን ለማስፋት ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እና ከሰ/ት/ቤቶች ጋር ውይይት ተደርጓል
  • ጠቅላላ ጉባኤ ተካሂዷል (መለስተኛ ዐውደ ርዕይም ተዘጋጅቶ ነበር)

ከ፳፻፮-፳፻፲ ዓ.ም. የተከናወኑ ዐበይት ተግባራት

  • ደቡብ አፍሪካውያን ካህናት ኢትዮጵያ ተልከው ሥልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል
  • በጆሐንስበርግ የነበረው አገልግሎት እንደገና መጠናከር የጀመረበት ወቅት ነበር (ለጸሎት ቦታ ተፈቅዷል፤ የጠቅላላ ጉባኤ በጆሐንስበርግ ተደርጎ የሥራ አስፈጻሚ ተመርጧል)
  • ለጉባኤያት መምህራንን በመላክና፣ በሩቅ ላሉ ምእመናን ቅዳሴ በቨርቿል በበማስተላልፍ ሐዋርያዊ አገልግሎቱ ቀጥሎ ነበር
  • የአብያተ ክርስቲያናት እና የጉባኤያት የዳሠሣ ጥናት ንድፈ ሐሳብ ቀርቦ ጸድቋል
  • ከሰ/ት/ቤቶች ጋር በመተባበር የሕፃናት እና አዳጊዎች ትምህርት በአንዳንድ አጥቢያዎች የተጀመረበት ጊዜ ነበር
  • መጽሐፈ ግጻዌ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ ለመተርጐም ሥራ የተጀመረበት ጊዜ ነበር
  • የግንቦት ልደታ እና የማኅበሩን የምሥረታ በዓል በደማቅ ኹኔታ ማክበር ተጀምሯል
  • የሕትመት ውጤቶችን የማሠራጨት ሥራም ተጠናክሮ ቀጥሎ ነበር

በ፳፻፲፩ ዓ.ም. የተከናወኑ ዐበይት ተግባራት

  • ግ/ጣቢያውን ለማጠናከር ከተለያየ ቦታ ከተገኙ አባላትና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል
  • አባላት በተለያዩ የአገልግሎት ክፍሎች ገብተው እንዲያገለግሉ ተደርጓል
  • የሕፃናት እና አዳጊዎችን ትምህርት ለማጠናከር ከሰ/ት/ቤቶች ጋር በመኾን ሥርዐተ ትምህርት እና የሥነ ምግባር መመሪያ ተዘጋጅቷል፣ መምህራንና ወላጆችን የሚያስተባብር ኮሚቴ ተዋቅሯል
  • የጉዞ መርሐ ግብራትን በማካሔድ እና የግንቦት ልደታን በዓል ከምእመናን ጋር በማክበር አግልግሎቱ ቀጥሎ ነበር
  • ሲተርጐም የነበረው መጸሐፈ ግጻዊ በሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ተመርቋል

በ፳፻፲፪ ዓ.ም. የተከናወኑ ዐበይት ተግባራት

  • አባላትን በደንብ በማሰባሰብ አገልግሎቱን ለማጠናከር የሥራ አስፈጻሚ አባላትን ከፕሪቶርያና ጆሐንስበርግ ከሚገኙ አባላት በመምረጥ አገልግሎቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተደርጓል
  • ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍሎች ተጨምረው አገልግሎቱ በደንብ የሰፋበት ጊዜ ነበር
  • በኮቪድ ወረርሽኝ ጊዜ በርቀት (Virtual) የጸሎት፣ የምክርና የትምህርት አገልግሎት ተሰጥቷል፣ በወረርሽኙ ወቅት ለአድባራትና ለምእመናን የ75 ሺህ ራንድ ድጋፍ ተደርጓል
  • ሕፃናት እና አዳጊዎችን በተለያየ ደረጃ በዕድሜ በመለየት በርቀት (Virtual) በተጠናከረ መልኩ ትምህርት መስጠት የተጀመረበት ጊዜ ነበር
  • የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎችን በርቀት (Virtual) ማስተማር የተጀመረበት ጊዜ ነበር
  • የሕትመት ውጤቶችን ሥርጭት በተጠናከረ መልኩ ተካሒዷል (የሐመር መጽሔት፣ ስምዐ ጽድቅ፣ መንፈሳዊ መጻሕፍትን) በተጠናከረ መልኩ ያሠራጩ ነበር
  • አድባራትና ጉባኤያት ያሉበትን ኹኔታ ለማወቅ የዳሠሣ ጥናት ተደርጓል

በ፳፻፲፫ ዓ.ም. የተከናወኑ ዐበይት ተግባራት

  • ግ/ጣቢያውን በደቡብ አፍሪካ ሕግ አስመዝግቦ የባንክ ሒሳብ ቊጥር ማስከፈት ተችሏል
  • በጆሐንስበርግና በፕሪቶሪያ ያሉ አባላት በአንድ የሥራ አስፈጻሚ መካተታቸው አገልግሎቱ እንዲጠናከር እገዛ አድርጓል
  • ለሥራ አስፈጻሚ አባላት በተለያዩ ጉዳዮች ሥልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል (የአመራር፣ በፋይናንስ አያያዝ፣ በኦዲት እና ኢንስፔክሽን)
  • የአባላትን ተሳትፎ ለማጠናከር ልምድ ያላቸውን አባላት በመጋበዝ (በአገልግሎት፣ በመንፈሳዊ ሕይወት፣ በንስሐ ሕይወትና ሰዓት አጠቃቀም ዙሪያ) ውይይት ተደርጓል
  • ምእመናን ስለ ቤተክርስቲያን ያላቸውን እውቀት ለማስፋት ዐውደ ርዕይ በጆሐንስበርግና በፕሪቶርያ ተዘጋጅቷል
  • ከሀ/ስብከቱ እና ከሌሎች ክፍለ ዓለማት ጋር በመቅናጀት በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ለምእመናን የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶች ተደርገዋል
  • በክፍለ-ሀገራት ለሚኖሩ ምእመናን ለዐበይት በዐላት የቅዳሴ ሥርዐትን በማስተላለፍ የስብከተ ወንጌልን ተደራሽነት የማስፋት ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሎ ነበር
  • ወደ ፍሪናኬ ማሕደረ ስብሐት ቅደስት ልደታ ማርያም ቤተ ክርስቲያ ልዩ  የኾነ ሐዊረ ሐይወት ተደርጓል
  • ሐዋርያዊ አገልግሎት ለማጠናከር ለካህናትና መምህራን የተለያየ ሥልጠና ተሰጥቷል (በእንግሊዝኛ እና በዐማርኛ ቋንቋ)
    • ለዐራት ደቡብ አፍሪካዊያን ካህናትን የደረጃ አንድ የመምህራን ሥልጠና ተሰጥቷል
    • ኹለት ደቡብ አፈሪካዊ ካህናት የዲፕሎማ ዕድል እንዲያገኙ ተደርጓል
    • ለአባላት የመርሐ ግብር አመራር ሥልጠና በመስጠት እና ወደ ሥራ በማስገባት  ሐዋርያዊ አገልግሎትን መደገፍ ተችሏል
  • የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችን በመለየት (ለወላጆች፤ ለነጋዴያን፣ ላላገቡ) ትምህርትና ሥልጠና  በመስጠት መንፈሳዊ ህይወታቸውን እንዲያጎለብቱ ተደርጓል
  • የግንቦት ልደታን በዓል ከምእመናን ጋር በፕሪቶሪያና በጆሐንስበርግ በደማቅ ኹኔታ በማክበር ከበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደርጓል