ከ፲፱፻፺፭– ፳፻ዓ.ም
- ሱቅከፍተው የተለያዩ ገቢ የሚያስገኙ የልማት ሥራዎችን ያከናውኑ ነበር
- ከአባላትወርኃዊ አስተዋጽኦ እየተሰበሰበ 40% ወደ ዋናው ማእከል ይልኩ ነበር
- የተወሰኑአባላት ምእመናንን በማስተምሩ ይሳተፉ ነበር
ከ፳፻፩ – ፳፻፫ ዓ.ም
- ፕሪቶሪያ ያሉ አባላት በዐርብ ጸሎትና በማክሰኞ ጉባኤን ላይ በመካፈል የፕሪቶሪያ ሐመረ ኖኅ ቅ/ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያንን የመደገፍ ሥራ ይሠሩ ነበር
- ደቡብአፍሪካውያን ካህናት ኢትዮጵያ ሒደው ሥልጠና እንዲያገኙ አግዘዋል
- ለጉባኤያትመምህራንን በመላክ ስብከተ ወንጌል እንዲስፋፋ አስተዋጽኦ አድርገዋል
በ፳፻፭ ዓ.ም. የተከናወኑ ዐበይት ተግባራት
- በወቅቱ ብዙ አባላትም ወደ ግ/ጣቢያው የመጡበት ጊዜ ነበር
- ተቀዛቅዞ የነበረውን በጆሐንስበርግ አገልግሎት ለማጠናከር ውይይት ተደርጓል
- የሥራ አስፈጻሚ አባላት ምርጫ ተካሂዷል፤ በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ አባላት ሥራ አስፈጻሚ ውስጥ እንዲካታቱ ተደርጓል
- የሥራ አስፈጻሚ አባላት (ሰብሳቢ፣ ም/ሰብሳቢ፣ ጸሓፊ፣ ግንኙነት፣ ልማት፣ ትምህርት፣ ሒሳብ እና ኦዲትና ኢንስፔክሽን ክፍላት) ተመርጠዋል
- ክፍሎች በየሁለት ሳምንቱ በስካይፕ ስብሰባ ያደርጉ ነበር
- የግ/ጣቢያውን የአገልግሎት ለማጠናከርና ተደራሽነቱን ለማስፋት ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እና ከሰ/ት/ቤቶች ጋር ውይይት ተደርጓል
- ጠቅላላ ጉባኤ ተካሂዷል (መለስተኛ ዐውደ ርዕይም ተዘጋጅቶ ነበር)
ከ፳፻፮-፳፻፲ ዓ.ም. የተከናወኑ ዐበይት ተግባራት
- ደቡብ አፍሪካውያን ካህናት ኢትዮጵያ ተልከው ሥልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል
- በጆሐንስበርግ የነበረው አገልግሎት እንደገና መጠናከር የጀመረበት ወቅት ነበር (ለጸሎት ቦታ ተፈቅዷል፤ የጠቅላላ ጉባኤ በጆሐንስበርግ ተደርጎ የሥራ አስፈጻሚ ተመርጧል)
- ለጉባኤያት መምህራንን በመላክና፣ በሩቅ ላሉ ምእመናን ቅዳሴ በቨርቿል በበማስተላልፍ ሐዋርያዊ አገልግሎቱ ቀጥሎ ነበር
- የአብያተ ክርስቲያናት እና የጉባኤያት የዳሠሣ ጥናት ንድፈ ሐሳብ ቀርቦ ጸድቋል
- ከሰ/ት/ቤቶች ጋር በመተባበር የሕፃናት እና አዳጊዎች ትምህርት በአንዳንድ አጥቢያዎች የተጀመረበት ጊዜ ነበር
- መጽሐፈ ግጻዌ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ ለመተርጐም ሥራ የተጀመረበት ጊዜ ነበር
- የግንቦት ልደታ እና የማኅበሩን የምሥረታ በዓል በደማቅ ኹኔታ ማክበር ተጀምሯል
- የሕትመት ውጤቶችን የማሠራጨት ሥራም ተጠናክሮ ቀጥሎ ነበር
በ፳፻፲፩ ዓ.ም. የተከናወኑ ዐበይት ተግባራት
- ግ/ጣቢያውን ለማጠናከር ከተለያየ ቦታ ከተገኙ አባላትና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል
- አባላት በተለያዩ የአገልግሎት ክፍሎች ገብተው እንዲያገለግሉ ተደርጓል
- የሕፃናት እና አዳጊዎችን ትምህርት ለማጠናከር ከሰ/ት/ቤቶች ጋር በመኾን ሥርዐተ ትምህርት እና የሥነ ምግባር መመሪያ ተዘጋጅቷል፣ መምህራንና ወላጆችን የሚያስተባብር ኮሚቴ ተዋቅሯል
- የጉዞ መርሐ ግብራትን በማካሔድ እና የግንቦት ልደታን በዓል ከምእመናን ጋር በማክበር አግልግሎቱ ቀጥሎ ነበር
- ሲተርጐም የነበረው መጸሐፈ ግጻዊ በሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ተመርቋል
በ፳፻፲፪ ዓ.ም. የተከናወኑ ዐበይት ተግባራት
- አባላትን በደንብ በማሰባሰብ አገልግሎቱን ለማጠናከር የሥራ አስፈጻሚ አባላትን ከፕሪቶርያና ጆሐንስበርግ ከሚገኙ አባላት በመምረጥ አገልግሎቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተደርጓል
- ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍሎች ተጨምረው አገልግሎቱ በደንብ የሰፋበት ጊዜ ነበር
- በኮቪድ ወረርሽኝ ጊዜ በርቀት (Virtual) የጸሎት፣ የምክርና የትምህርት አገልግሎት ተሰጥቷል፣ በወረርሽኙ ወቅት ለአድባራትና ለምእመናን የ75 ሺህ ራንድ ድጋፍ ተደርጓል
- ሕፃናት እና አዳጊዎችን በተለያየ ደረጃ በዕድሜ በመለየት በርቀት (Virtual) በተጠናከረ መልኩ ትምህርት መስጠት የተጀመረበት ጊዜ ነበር
- የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎችን በርቀት (Virtual) ማስተማር የተጀመረበት ጊዜ ነበር
- የሕትመት ውጤቶችን ሥርጭት በተጠናከረ መልኩ ተካሒዷል (የሐመር መጽሔት፣ ስምዐ ጽድቅ፣ መንፈሳዊ መጻሕፍትን) በተጠናከረ መልኩ ያሠራጩ ነበር
- አድባራትና ጉባኤያት ያሉበትን ኹኔታ ለማወቅ የዳሠሣ ጥናት ተደርጓል
በ፳፻፲፫ ዓ.ም. የተከናወኑ ዐበይት ተግባራት
- ግ/ጣቢያውን በደቡብ አፍሪካ ሕግ አስመዝግቦ የባንክ ሒሳብ ቊጥር ማስከፈት ተችሏል
- በጆሐንስበርግና በፕሪቶሪያ ያሉ አባላት በአንድ የሥራ አስፈጻሚ መካተታቸው አገልግሎቱ እንዲጠናከር እገዛ አድርጓል
- ለሥራ አስፈጻሚ አባላት በተለያዩ ጉዳዮች ሥልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል (የአመራር፣ በፋይናንስ አያያዝ፣ በኦዲት እና ኢንስፔክሽን)
- የአባላትን ተሳትፎ ለማጠናከር ልምድ ያላቸውን አባላት በመጋበዝ (በአገልግሎት፣ በመንፈሳዊ ሕይወት፣ በንስሐ ሕይወትና ሰዓት አጠቃቀም ዙሪያ) ውይይት ተደርጓል
- ምእመናን ስለ ቤተክርስቲያን ያላቸውን እውቀት ለማስፋት ዐውደ ርዕይ በጆሐንስበርግና በፕሪቶርያ ተዘጋጅቷል
- ከሀ/ስብከቱ እና ከሌሎች ክፍለ ዓለማት ጋር በመቅናጀት በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ለምእመናን የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶች ተደርገዋል
- በክፍለ-ሀገራት ለሚኖሩ ምእመናን ለዐበይት በዐላት የቅዳሴ ሥርዐትን በማስተላለፍ የስብከተ ወንጌልን ተደራሽነት የማስፋት ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሎ ነበር
- ወደ ፍሪናኬ ማሕደረ ስብሐት ቅደስት ልደታ ማርያም ቤተ ክርስቲያ ልዩ የኾነ ሐዊረ ሐይወት ተደርጓል
- ሐዋርያዊ አገልግሎት ለማጠናከር ለካህናትና መምህራን የተለያየ ሥልጠና ተሰጥቷል (በእንግሊዝኛ እና በዐማርኛ ቋንቋ)
- ለዐራት ደቡብ አፍሪካዊያን ካህናትን የደረጃ አንድ የመምህራን ሥልጠና ተሰጥቷል
- ኹለት ደቡብ አፈሪካዊ ካህናት የዲፕሎማ ዕድል እንዲያገኙ ተደርጓል
- ለአባላት የመርሐ ግብር አመራር ሥልጠና በመስጠት እና ወደ ሥራ በማስገባት ሐዋርያዊ አገልግሎትን መደገፍ ተችሏል
- የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችን በመለየት (ለወላጆች፤ ለነጋዴያን፣ ላላገቡ) ትምህርትና ሥልጠና በመስጠት መንፈሳዊ ህይወታቸውን እንዲያጎለብቱ ተደርጓል
- የግንቦት ልደታን በዓል ከምእመናን ጋር በፕሪቶሪያና በጆሐንስበርግ በደማቅ ኹኔታ በማክበር ከበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደርጓል