የደቡባዊ አፍሪካ ማእከል

የደቡብ አፍሪካ /ጣቢያ አመሠራረት

 • በ፲፱፻፺፬.. 
  • በጆሐንስበርግ የሚገኙ ወንድሞች እና እኅቶች የጋራ ጸሎት ያደርጉ እና ይማማሩ ነበር
  • የሐመር መጽሔት እና የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ በማምጣት ያከፋፍሉ ነበር
  • መንፈሳዊ ጉባኤያትን በማስተባበር እና በማስተማርም ንቁ ተሳትፎ ያደርጉ ነበር
  • አብያተ ክርስቲያናት በሚገዙበት ወቅት በማስተባበር እና ገንዘብ በማሰባሰብ ይሳተፉ  ነበር
  • በፖርት ኤልሳቤጥ የሚገኙ ደቡብ አፍሪካዊ ኦርቶዶክሳውያንን የመጎብኘት እና የማጽናናት ሥራም ላይ ይሳተፉ ነበር
  • መምህራን ከሀገር ቤት በማስመጣት ስብከተ ወንጌል እንዲስፋፋ እግዛ ያደርጉ ነበር
 • በ፲፱፻፺፭.. የደቡብ አፍሪካ ልዩ ግንኙነት ጣቢያ በጆሐንስበርግ ተቋቋመ
 • በ፳፻፩.. የተወሰኑ አባላት ወደ ሌላ ቦታ መዛወራቸውና በነበሩ አንዳንድ ችግሮች ጆሐንስበርግ አገልግሎት  በማዳከሙ ምክንያት የግ/ጣቢያው ጽ/ቤት ወደ ፕሪቶሪያ እንዲዛወር ተደርጓል