• እንኳን በደኅና መጡ !

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ

ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ በዓመት ሁለት ጊዜ በጥቅምትና በግንቦት እንደምታካሂድ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት የግንቦቱ ርክበ ካህናት ትንሣኤ በዋለ ከ፳፭ኛው ቀን ጀምሮ ግንቦት ፲፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በጸሎት የተጀመረ ሲሆን ግንቦት ፲፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም በብፀዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም […]

“ፋሲካችን ክርስቶስ ተሠውቶ የለምን?”( ፩ኛቆሮ.፭፥፯)

በቀሲስ ኃይለ ሚካኤል ብርሃኑ ፋሲካ ማለት ማለፍ፣ መሻገር፣ ደስታ  ሲሆን በዕብራይስጥ  “ፓሳሕ” ይለዋል፡፡ ይህም ዐለፈ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድም በትንሣኤ በዓል የሚዘመረውን የመዝሙር ክፍል “ፋሲካ” በማለት ሰይሞታል፡፡ ይኸውም “ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐፂባ በደመ ክርስቶስ፤ ምድርም በክርስቶስ ደም ታጥባ ፋሲካን ታደርጋለች” በማለት እንደተናገረው እኛም እርሱን አብነት አድርገን በእርሱ ዜማ እያመሰገንን ትንሣኤውን እየመሰከርን በትንሣኤውም ያገኘነውን ትንሣኤ ዘለ […]

የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ

ክፍል አንድ መ/ር ሕሊና በለጠ የክርስቶስ ሞቶ መነሣት ለትንሣኤያችን መጀመሪያ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱና በትንሣኤው ትንሣኤያችንን ባያረጋግጥልን ኖሮ ሃይማኖት ዋጋ አያሰጥም ነበር፡፡ የአማኞችም ሕይወታቸው በክርስቶስ ሞትና በትንሣኤው በተገኘ ሕይወት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ለዚህም ነው የጥንት ክርስቲያኖች “ማራናታ” እያሉ ሰላምታ ይለዋወጡ የነበሩት፡፡ “ማራናታ” ማለት “ክርስቶስ የተነሣው፣ ያረገውና ዳግም የሚመጣው” ማለት ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያናችንም ይህ […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን