• እንኳን በደኅና መጡ !

ራስን መግዛት

በመ/ር በትረ ማርያም አበባው(የመጻሕፍተ ብሉያትና የመጻሕፈተ መነኮሳት መምህር) ራስን መግዛት ማለት ራስን ከክፉ ነገር መጠበቅ፣ ሰውነትን መቆጣጠር፣ ራስን ከኃጢኣት ማራቅ ማለት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች በላከው መልእክቱ ራስን መግዛት የመንፈስ ፍሬ እንደሆነ ገልጧል። (ገላ. ፭፥፳፪) ቅዱስ ጴጥሮስም በ(፪ኛ ጴጥ.፩፣፮) “በበጎነትም ዕውቀትን በዕውቀትም ራስን መግዛትን ራስንም በመግዛት መጽናትን በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችነትን መዋደድ […]

ከፊት ይልቅ ትጉ (፪ኛ.ጴጥ. ፩፥፲)

በመጋቤ ሃይማኖት መ/ር  ምትኩ አበራ ይህንን ኃይለ ቃል የተናገረው ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ነው፡፡ ኃይለ ቃሉን የምናገኘው ደግሞ በ፪ኛ ጴጥ.፩፥፭-፲፩ ላይ ነው፡፡ ሙሉው ንባብ እንዲህ ይላል፡- “… ስለዚህ ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፤ በበጎነትም ዕውቀትን፤ በዕውቀትም ራስን መግዛት፤ ራስንም በመግዛት መጽናትን፤ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፤ እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፤ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ፤ እነዚህ […]

ግቢ ጉባኤያት እና የጊዜ አጠቃቀም

በእንዳለ ደምስስ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ይጠቀሙበት ዘንድ ከሰጣቸው ሥጦታዎች ውስጥ አንዱ ጊዜ ነው፡፡፡ ሁሉንም በሥርዓት አበጅቶታልና የተሰጠውን ሥጦታ በአግባቡ የመያዝና የመጠቀም ኃላፊነት ደግሞ ከሰው ልጆች ሁሉ ይጠበቃል፡፡ “የሠራው ሥራ ሁሉ በጊዜው መልካም ነው” እንዲል (መክ.፫፥፲፩)፡፡ ጊዜ ቆሞ አይጠብቀንም፡፡ ሴኮንድ ወደ ደቂቃ፣ ደቂቃ ወደ ሰዓት፣ ሰዓታት ወደ ቀን፣ ቀን ወደ ሳምንት፣ ሳምንታት ወደ ወራት፣ ወራት ወደ […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን