• እንኳን በደኅና መጡ !

“ግንቦት ልደታን ለግቢ ጉባኤያችን”

ማኅበረ ቅዱሳን የተመሠረተበትን ፴፩ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ “ግንቦት ልደታን ለግቢ ጉባኤያችን” በሚል መሪ ቃል ከሚያዚያ ፳፰ እስከ ግንቦት ፮ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም በልዩ ልዩ መርሐ ግብሮች እንደሚከበር ዐቢይ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ባለፉት ፴፩ ዓመታት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት መሠረት ሥርዓተ ትምህርት ቀርጾ በማስተማር በዕውቀት እና […]

ከትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ዕለታት ስያሜዎች

ከትንሣኤ እስከ ዳግም ትንሣኤ ባለው አንድ ሳምንት ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ሰባቱን ዕለታት የተለያዩ ምሥጢራዊ ስያሜዎችን ሰጥታ ሐዋርያዊ አገልግሎቷን ታከናውንባቸዋለች፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ቤዛ አድርጎ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ፣ ሞቶ፣ ተቀብሮ፣ ሙስና መቃብር ሳይወስነው መግነዝ ፍቱልኝ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በሞቱ ሞትን ሽሮ በትንሣኤው ትንሣኤያችንን አውጇልና ኦርቶዶክሳውያን በልዩ ድምቀት የሳምንቱን ዕለታት እናከብራለን፡፡ […]

“ዳግመኛ ልትወለዱ ይገባችኋል” (ዮሐ. ፫፥፯)

ይህንን ቃል የተናገረው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአይሁድ መምህር ለሆነው ኒቆዲሞስ በጥምቀት ዳግመኛ ያልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርስ እንደማይችል ባስረዳበት ትምህርቱ ነው፡፡ ኒቆዲሞስ ምንም እንኳን የአይሁድ መምህር ቢሆንም ምሥጢሩን እያመሠጠረ የኦሪትን ትምህርት ቢያስተምርም ስለ ዳግም መወለድ ምሥጢር ተሠውሮበት ጌታችንን ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ሲጠይቅ እንመለከታለን፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ለሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ሲመላለስ ኢአማንያንን […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን