• እንኳን በደኅና መጡ !

ኦርቶዶክሳዊ የአለባበስ ሥርዓት

ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮዋ የሰው ሕይወትን በመልካም ጎዳና በሥጋም ሆነ በነፍስ የሚመራ ነው፡፡ ትምህርትዋም ፍጹም መንፈሳዊ ነው፡፡ የምታስተምረውም የአምላክዋን ቃል በቀጥታ ሳትቀንስ እና ሳትጨምር ሳታስረዝምና ሳታሳጥር ለሚሰማት ሁሉ ታደርሳለች፡፡ የሥርዓትዋም መነሻ እና መድረሻ ከምድር ሳይሆን ከሰማይ ነው፡፡ “ሥርዓተ ሰማይ ተሠርዐ በምድር” እንዲል፡፡ ይህም ሰማያዊውን ሥርዓት ተከትላ በምድር ያሉ አባላቶቹዋ የሰማዩን ሥርዓት በእምነት በመመልከት በምድር […]

“ሁሉን መርምሩ መልካሙን ያዙ” (፩ኛተሰ. ፭፥፳፩)

ይህ መልእክት የጥናትን ምርምርን አስፈላጊነት ከምንረዳባቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ኃይለ ቃላት አንዱ ሲሆን በአካባቢያችን የምናገኛቸው በርካታ መልካም እና መልካም ያልሆኑ ነገሮችን መርምረን (ተመራምረን) ፈትነን መልካም የሆነውን ያውም የሚጠቅመንን ብቻ እንድንይዝ የተመከርንበት ኃይለ ቃል ነው፡፡ ምርምር ለእኛ በእግዚአብሔር ለምናምን ሰዎች አዲስና እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ ቀደምት አባቶቻችን መርምረው (ተመራምረው) ችግሮቻቸውን ፈትተዋል፤ በርካታ ሥራዎችንም ሠርተዋል፡፡ ከኢአማኒነት ወደ አማኒነት የመጡ […]

ጽዮን ማርያም

“እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ።” (መዝ. ፻፴፩፥፲፫-፲፬) እንዲል ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በመዝሙሩ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማናዊት የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነችውን የእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ዓመታዊ በዓል ኅዳር ፳፩ ቀን በድምቀት ታከብራለች፡፡ “ጽዮን” ማለት “አምባ፣ መጠጊያ” ማለት ነው፡፡ “ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፤ በውስጥዋም ሰው ተወለደ” (መዝ. ፹፮፥፭) […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን