• እንኳን በደኅና መጡ !

“ኦ ዝ መንክር ልደተ አምላክ እማርያም እምቅድስት ድንግል አግመረቶ ለቃል ኢቀደሞ ዘርዕ ለልደቱ” (ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ)

በመ/ር ታዴዎስ መንግስቴ የእግዚአብሔር ሰው የመሆን ምሥጢር በሰው አእምሮ አይደለም በመላእክት ኅሊናም ለመረዳት የማይቻል ረቂቅ፣ የማይመረመር ምሥጢር፣ የማይደረስበት ሩቅ፣ ዝም ብለው የሚያደንቁት ግሩም ነው። ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ድንግል ማርያምን ባመሰገነበት ውዳሴው “ኦ ዝ መንክር ልደተ አምላክ እማርያም እምቅድስት ድንግል አግመረቶ ለቃል ኢቀደሞ ዘርዕ ለልደቱ፤ ልዩ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅ፣ ቃልን ወሰነችው […]

“የምናመልከው አምላክ ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል” (ዳን. ፫፥፲፯)

ገብርኤል ማለት “እግዚእ ወገብር፤ የእግአብሔር አገልጋይ” ማለት ነው። እግዚአብሔር ሥነ ፍጥረት መፍጠር በጀመረበት በዕለተ እሑድ ስምንት ፍጥረታትን ፈጥሯል፡፡ ከእነዚህም መካከል ቅዱሳን መላእክት ተፈጥረዋል፡፡ አገልግሎታቸውም ሳያቋርጡ እግዚአብሔርን “ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ” እያሉ ማመስገን ነው፡፡ እግዚአብሔርም መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላም ተሰወራቸው፡፡ በመላእክቱም ከተማ “መኑ ፈጠረነ፡ ማን ፈጠረን?” እያሉ ፈጣሪያቸውን ፍለጋ ጥረት አደረጉ፡፡ ነገር ግን ምላሽ ማግኘት ባለመቻላቸው ከመላእክቱ መካከል ሳጥናኤል በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ማጋረጃውን የመክፈትና የመዝጋት ክብር ተሰጥቶታልና ወደ ላይ […]

መንፈሳዊ ብስለት

መንፈሳዊ ብስለት ማለት አንድ ክርስቲያን በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ የሚያመጣው መንፈሳዊ እድገት ነው። መንፈሳዊ እድገት (ብስለት) የሚመጣው ደግሞ ከአካላዊ ተግባር፣ ከልቡናዊ የሐሳብ ጽርየት (ልቡናን ከክፉ ነገር ከማንጻት)፣ ከዐቂበ ርእስ እም ኃጢአት (ራስን ከገቢረ ኃጢአት መጠበቅ) ወዘተ … ነው ። ሰው መንፈሳዊ እድገት ጀመረ የሚባለው ሃይማኖቱን ተረድቶት፣ ፍቅረ እግዚአብሔር ገብቶት ሁሉንም ጉዳይ ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ብሎ ማድረግ […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን