“እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።”
፩ኛ ዜና መዋዕል ፲፮፥፲፩
በዲያቆን በረከት አዝመራው
እግዚአብሔርን መፈለግ እና ወደ እርሱ ሰው ሁሉ መቅረብ ይገባዋል? ወይስ ጥቂቶች ብቻ የሚጣጣሩበት ሕይወት ነው ብለን እንደፈለግን መሆን ይቻለናል? በውኑ አእምሮ ያለው ፍጡር ያስገኘውን ፈጣሪውን ከመፈለግ፣ ከፈጣሪው ጋር ኅብረት ከመፍጠር እና የተፈጠረበትን ዓላማ ከመፈጸም የበለጠ ምን ታላቅ ተግባር አለው?
መልካም አባት ሁልጊዜ ለልጁ ጥሩ ነገርን እንደሚያስብ እና እንደሚያደርግ የታወቀ ነው። በዚህም ምክንያት “ጤነኛ” ልጅ ሁሉ አባቱን ይወዳል:: ካለማወቅ እና ከድካም የተነሳ አንዳንድ ጊዜ ቢሳሳትም በአብዛኛው ግን የአባቱን ትእዛዝ ይጠብቃል:: ታዲያ እግዚአብሔር “ከልብ ለሚፈልጉኝ ሁሉ እገኛለሁ፤ ከምድራውያን ወላጆች ጋር የማልነጻጸር መልካም አባት ነኝ፤ ለሚወዱኝ ዓይን ያላየው፣ ጆሮ ያልሰማው፣ በሰው ልብ ያልታሰበ ታላቅ ሥጦታን እሰጣለሁ” (፪ኛ ዜና መዋዕል ፲፭፥፪፣ ማቴ. ፯፥፲፩፣ ፩ኛ ቆሮ. ፪፥፱) እያለ ዘወትር እየተጣራ፤ ሰዎች ወደ እርሱ በሙሉ ልብ ለመቅረብ ፈቃዳችን የሚደክመው እና ዳተኛ የምንሆነው ለምንድን ነው? Read more