• እንኳን በደኅና መጡ !

ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ

ቅዱስ ያሬድ ውልደትና እድገቱ ኢትዮጵያ ወስጥ ፤ አክሱም ከተማ ከአባቱ ከአብዩድና ከእናቱ ታውክሊያ ነው ፤ ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስ እናቱ መምህር ወደ ሆነው አጎቱ አባ ጌዲዬን ትወስደዋለች፡፡እርሱ ግን በመጀመሪያ ትምህርት ሊገባው አልቻለም፡፡ ከዕለታት በአንድ ቀን መምህር ጌዲዬን ያሬድን ሲገርፈው በምሬት አለቀሰ ፤ ማይኪራህ ወደምትባል ቦታም ተጓዝ፤

እብድ መነኲሲት

ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ  ክርስቶስ ውለታና ፍቅር ራሷን እብድ  ያደረገችው መነኲሲት ቅዱስ ጳኩሚስ ከመሠረታቸው የታቤኔዝ (ታቤኔሲዮት) ገዳማት መካከል ከወንዶች ገዳማት ራቅ ብሎ የተመሠረተ የሴቶች ገዳም ነበር። በዚያም ውስጥ አራት መቶ ሴቶች መነኮሳይያት ይኖሩ ነበር። በዚያ ገዳም ውስጥ ራሷን እንዳበደችና ርኲስ መንፈስ እንደያዛት የምታስመስል ድንግል ሴት ነበረች። ሌሎቹ እርሷን ከመጸየፋቸው የተነሣ አብረዋት እንኳን አይበሉም ነበር ፤ […]

አንፀባራቂና የደስታ በዓል

እግዚአብሔርን የሚያምንና የሚወድ ቢኖር ፥ እርሱ በዚህ አንፀባራቂና የደስታ በዓል ደስ ይበለው፡፡ ብልህ አገልጋይ ቢኖር ፥ እርሱ ወደ ጌታው ሐሴት ገብቶ እልል ይበል፡፡ በጾም የደከመ ቢኖር፥ አሁን ደመወዙን ይቀበል፡፡ በመጀመሪያው ሰዓት ወደ አምላኩ የቀረበ ቢኖር ፥ ዛሬ ሽልማቱን ይውሰድ፡፡

በሦስተኛው ሰዓት የመጣ ቢኖር ፥ እርሱ በዓሉን በምስጋና ያክብር፡፡