መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
በመቅረዝ ላይ የተቀመጠች መብራት
ከመቅረዜ ላይ አድርጌ ለኮስኳት፡፡ እርሷም ቦገግ ብላ አበራችልኝ፡፡ ከመብራቷ የሚወጣውን ብርሃን ስመለከት ውስጤ ሰላም ይሰማኛል፤ ተስፋም አገኛለሁ፤ በጨለማ ውስጥ መብራት ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ በጭንቅ፣ በመረበሽ እና በሁከት ተወጥሮ ለሚጨነቅ አእምሮዬ ወገግ ብላ እንደምታበራ ብርሃኔ ሆነችኝ፡፡…
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ
የአምላክ እናት መገለጥ!
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ‹‹በዓለ ደብረ ምጥማቅ›› አደረሳችሁ!
አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ስለ መታየቱ የክርስቲያን ወገኖች ሁላችንም ታላቅ በዓልን እናደርጋለን።
‹‹ነገን ዛሬ እንሥራ››
ተወዳጆች! እንዴት ሰነበታችሁ? እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ!
በክፍል ስድስት “ክብረ ምንኩስና ትናንት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የነበረውን ክብርና ሞገስ ያስገኘውን የቅድስና ፍሬና ያሳረፈውን አሻራ” አንስተን ለመዳሰስ ሞክረናል፡፡
በዚህ በክፍል ሰባት ደግሞ ምንኩስና ዛሬ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እያጋጠመው ያለውን ተግዳሮት ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡ ቀደም ብለን እንደ ተመለከትነው ምንኩስና ከምድራዊው ይልቅ ሰማያዊውን፣ ከሰው ይልቅ የመላእክትን ግብር መምረጥ፣ ፍጹም ሆኖ ፍጹም የሆነችውን መንግሥት ለመውረስ ሁሉን ትቶ መመነን፣ ከሰው ከዓለም መለየት፣ በገዳም በአጽንዖ በአት፣ በግብረ ምንኩስና መወሰን መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይሁን እንጅ በዘመናችን ምንኩስና በዘርፈ ብዙ ተግዳሮት ውስጥ ይገኛል፤ የተወሰኑ ችግሮችን ለማሳየት ያህል፡-
‹‹ሕፃናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተውአቸው፤ አትከልክሉአቸውም›› (ሉቃ.፲፰፥፲፮)
አእምሯቸው ብሩህ ልቡናቸው ንጹሕ የሆኑት ሕፃናት ተንኮል፣ ቂም፣ በቀል የሌለባቸው የዋሃን ናቸው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕፃናትን ወደ እርሱ እንዲያመጡ አድርጎ መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ እንደ እነርሱ (ሕፃናት) ተንኮል፣ ቂም፣ በቀልን በልቡና መያዝ እንደማያስፈልግ ከክፋት መራቅ እንዳለብን አስተማረባቸው፡፡
ወላጆች እንደ ልማዳቸው ለማስባረክ ሕፃናትን ወደ ጌታችን ሲያመጧቸው ደቀ መዛሙርቱ ‹‹ለምን አመጣችሁ!›› ብለው ወላጆችን በተናገሩ ጊዜ ጌታን ‹‹ተዋቸው›› አለ፤ ደቀ መዛሙርቱ መከልከላቸው ትምህርት ያስፈቱናል (ሕፃናት ናቸውና ይረብሻሉ) በማለት ነው፡፡ ጌታችን ግን እንዲመጡ አደረጋቸው፤ ባረካቸው፤ እነዚህ ሕፃናት ቁጥራቸው ከ፪፻ መቶ በላይ እንደሆነ መተርጉማነ አበው ያብራራሉ፤ በዚያን ጊዜ ከጌታችን የተባረኩት ሕፃናት አድገው ጳጳስ፣ ኤጲስ ቆጶስ ሆነዋል፤ ከፍጹምነት ማዕረግ ደርሰዋል፡፡ (የማቴዎስ ወንጌል አንድምታ ፲፱፥፲፭)
ምሥጢረ ጥምቀት
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን? የትንሣኤ በዓል እንዴት ነበር? ቤተ ክርስቲያን በመሄድ በማስቀደስ አከበራችሁተ አይደል! የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ በዓል የደስታ በዓላችን ነው! በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን በሠሩልን ሥርዓት መሠረት እስከ በዓለ ሃምሣ (ጰራቅሊጦስ) ይታሰባል፡፡
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! በሰንበት ትምህርት ቤት በመግባትም ተማሩ አገልግሉ፤ በቤተ እግዚአብሔር ማደግ መታደል ነውና! ሌላው ደግሞ በዘመናዊ ትምህርታችሁም በርቱ! ሁለተኛው የመንፈቀ ዓመት ትምህርት እየተገባደደ ስለሆነ በተማራችሁት መሠረትም ስለምትፈተኑ በርትታችሁ ማጥናት አለባችሁ፡፡ መልካም! አሁን ለዛሬ ወዳዘጋጀንላችሁ ትምህርት እናምራ፤ ባለፈው ምሥጢረ ሥጋዌን ተምረን ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ምሥጢረ ጥምቀትን እንማራለን፤ ተከታተሉን!
‹‹ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ነገር ሁሉ እናንተም አድርጉላቸው›› (ማቴ.፯፥፲፪)
በሕይወታችን ውስጥ ለአምላካችን እንዲሁም ለሌሎች ፍቅራችንን የምንገልጽበት መንገድ ለራሳችን እንደምናደርገውን ሁሉ ከልብ ከመነጨ ፍቃድ ለባልንጀሮቻችን ማድረግ ነው፡፡ መሠረታዊ ነገሮች እንዲሟሉልን ብቻ ሳይሆን ለምድራዊ ኑሮአችን የሚያስፈልጉንን ሁሉ ስናደረግ እንዲሁ ለቤተ ሰቦቻችን፣ ለወዳጆቻችን፣ ለዘመዶቻችን እና ለጎረቤቶቻችን ማድረግን መርሳት የለብንም፡፡ ይህም ማዕድ ከመጋራት ጀምሮ አብሮ እስከ መቸገር፣ መራቆትና ኅዝንንም ሆነ ደስታን እስከ መካፈል ይደርሳል፡፡
ከራድዮን
ከራድዮን ነጭ ወፍ ሲሆን በሊቃውንቱም ዘንድ የታወቀ ነው። ጠቢባን በድካም ፈልገው አድነው ይይዙታል፤ የታመመ ሰው ቢኖር ያቀርቡታል፤ እርሱም በሽተኛውን ትኩር ብሎ ያየዋል፤ የማይድን ለሞት የቀረበ ከሆነ ፊቱን አዙሮ ይመለሳል፤ ቀኑ ገና ከሆነ ግን አፉን ከፍቶ ከበሽተኛው አፍ እስትንፋሱን ይወስዳል፤ በልዑል እግዚአብሔር ኃይል የሰውየው ደዌ ሙሉ ለሙሉ ወደ ወፉ በእስትንፋሱ ይተላለፋል። ሰውየው ይድናል፤ ወፉ ይታመማል። ፊት ነጭ የነበረው እንደ ከሰል ይጠቁራል፤ ሕመም ሲሰማው ወደ አየር ይነጠቃል፤ ሲብስበት ወደ ባሕር ራሱን ይወረወራል። በባሕር ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ቆይቶ ጠጉሩን መልጦ በዐዲስ ተክቶ፣ ድኖ፣ታድሶ፣ ኃያል ሆኖ ይወጣል። ይህ ፍጥረት በዕለተ ሐሙስ የተፈጠረ ፍጥረታት ነው፡፡ ስለምን ፈጠረው? ቢሉ የወልደ እግዚአብሔር ክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ ለማያምኑ ትምህርት ምሳሌ አብነት ይሆን ዘንድ ይህን ወፍ የማዳን ኃይል ሰጥቶ ፈጥሮታል።
‹‹ነገን ዛሬ እንሥራ››
ውድ የእግዚአብሔር ቤተ ሰቦች! እንደምን ሰነበታችሁ? በዚህ ርእስ ቤተ ክርስቲያን ትናንት ለነበራት ድምቀት፣ ዛሬ ለገጠማት ተግዳሮት፣ ነገም ለሚኖራት ማንነት ክብረ ክህነትና ክብረ ምንኩስና የማይተካ አስተዋጽኦ እንዳላቸው እና እነዚህ ሁለት የክብረ ቤተ ክርስቲያን ምሰሶዎች የነገዋን ቤተ ክርስቲያን ሁኔታ ሊወስኑ እንደሚችሉ መንደርደሪያ ሐሳብ አንሥተን በመቀጠልም “ክብረ ክህነት ትናንት እንዴት ነበር? ዛሬስ ምን ሁኔታ ላይ ነው ? ነገስ ምን መሆን አለበት?” የሚሉ ጉዳዮችን ዳስሰን እስከ ክፍል አምስት አብረን ዘልቀናል፡፡ በክፍል ስድስትና ቀጣዮቹ ክፍሎች ደግሞ “ክብረ ምንኩስና ትናንት፣ ዛሬና ነገ ምን ይመስላልና መምሰል አለበት” የሚለውን እናጋራችኋለን፤ አብራችሁን ዝለቁ! መልካም ንባብ!
ምሥጢረ ሥጋዌ
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን! እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ! የትንሣኤ በዓል እንዴት ነበር? ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን በፈቃዱ በቅዱስ መስቀል ላይ ተሰቅሎ በመቃብር ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ከቆየ በኋላ ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፤ ይህች ዕለት ታላቅ ዕለት ናት! መልካም! አሁን ለዛሬ ወዳዘጋጀንላችሁ ትምህርት እናምራ፤ ባለፈው ምሥጢረ ሥላሴን ተምረን ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ስለ ምሥጢረ ሥጋዌ እንማራለን፤ ተከታተሉን!