መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::




ማይኪራህ
ከሌሊት ወፍ በመዓልቱ:
…… እልፍ እንቁላል ሊሰበሰብ፣
የወንዱ ጽንስ እንዲገፋ
…… ከበቅሎው ወተት ሊታለብ፤
ከማር ቀፎ የዝንብ መንጋ
…… አውሬው ጓዳ ገብቶ እንዲያድር፣
የተፈጥሮ ሕጉን ስቶ
…… ያለቦታው እንዲሰደር፤
ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ
ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ፣ የዜማ ደራሲና ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ድንቅ ተጋድሎን ፈጽሞ ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም የገባበት ዕለት ግንቦት ፲፩ የከበረች እንደመሆኗ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ታከብረዋለች፡፡
‹‹ኑ ምሳ ብሉ›› (ዮሐ.፳፩፥፲፪)
ይህን ኃይለ ቃል የተናገረው ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቃሉን ደግሞ የሚበላ ፈልገው ዓሣ ለማጥመድ ሌሊቱን ሲደክሙ ለነበሩ ግን የሚፈልጉትን ሳያገኙ በረኀብ ዝለው በፍለጋ ደክመው ለነበሩ ለቅዱሳን ሐዋርያት ነው፡፡ ሞትን በሞቱ ገድሎ፣ በትንሣኤው ትንሣኤያችንን አብሥሮ፣ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያት በጥብርያዶስ ባሕር ዳርቻ ተገለጠላቸው፤ ይህ ከትንሣኤው በኋላ ሲገለጥላቸው ሦስተኛው ጊዜ ነው፡፡ መጀመሪያ ሲገለጥላቸው አይሁድን ፈርተው በፍርሃት ተሸብበው በራቸውን ዘግተው በተስፋ መቁረጥ ውስጥ በነበሩ ጊዜ በዝግ ቤት ገብቶ ፍርሃትን አስወገደላቸው ተስፋቸውን ቀጠለላቸው፤ ለተረበሸው ልባቸው ‹‹ሰላም ለእናንተ ይሁን›› በማለት ሰላምን ሰጣቸው አረጋጋቸው፡፡ (ሉቃ.፳፬፥፴፮፣ዮሐ.፳፥፲፱)
“ትዋደዱ ዘንድ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ” (ዮሐ.፲፫፥፴፬)
መውደድ በሰዎች መካከል የሚኖር ስሜት ነው፤ ያለ መዋደድም በዚህ ምድር ላይ መኖር አይቻለንም፤ መጠኑ ይብዛም ይነስ በሰው ልብ ውስጥ የመዋደድ ስሜት ይፈጠራል፡፡ ሰዎች ተቻችለንና ተሳስብን እንዲሁም ተዛዝነን የምንኖረው ስንዋደድ ነው፡፡ ግን ይህ ስሜት ከምንም ተነሥቶ በውስጣችን ሊፈጠር አይችልምና መውደድ መነሻው ምንድነው? የሚለውን ነገር ብንመረምር መልካም ነው፡፡
”በቤተ ክርስቲያን ያጋጠሙ ችግሮች በዚህ ጥበብ ካልሆነ በቀር በመሳሳብና እልክ በመጋባት የሚፈቱ አይደሉም”
የቅዱስ ፓትርያርኩ የግንቦት ፳፻፲፭ ዓ.ም ርክበ ካህናት ጉባኤ መክፈቻ ንግግር
የትዕግሥት ፋና
ኢዮብ ጻድቅ ሰው ነው
ምክር የመከረ
ኢዮብ ፍጹም ሰው ነው
የትዕግሥት ፋና
በገድል የከበረ!
“የሕይወት ቀን” በግቢ ጉባኤያት
ወርቃማው የወጣትነት ዘመናችን በተስፋ፣ በመልካም ምኞትና በትጋት የተሞላ፣ ዕውቀትንና አቅምን ያማከለ ማንነታችን የሚታነጽበት፣ መንፈሳዊነታችን የሚገለጽበት የዕድሜ ክልል እንደመሆኑ የሕይወታችን መሠረት ነው፡፡ መንፈሳዊ ፍሬን አፍርተን ርስተ መንግሥተ ሰማያት ለምንወርስብትም የሕይወት ስንቅ የምንሰንቅበት የተጋድሎ ዘመን ስለመሆኑ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከልጅነታችን ጀምሮ አበክራ ታስተምረናለች፡፡ በሰንበት ትምህርት ቤቶቿም ኮትኩታ አሳድጋ መንፈሳዊ ፍሬ ለማፍራት ታበቃናለች፡፡ ለዚህ የመሸጋገሪያ ዕድሜ በደረስንበት ጊዜም የሕይወታችን መርሕ የሆነው ትምህርተ ወንጌል እንዳይጓደልብን በዐውደ ምሕረቷ ላይ ጉባኤ ዘርግታ ሰማያዊ ኅብስትን አዘጋጅታ ትመግበናለች፡፡
ግቢ ጉባኤያት በቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ጳውሎስ “ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና።” (፪ኛጴጥ. ፩፥፲) እንዲል በአእምሮ የጎለመሱ፣ በጥበብ ያደጉ፣ ዘመኑን የዋጁ የቤተ ክርስቲያንን ልጆች የበለጠ ማትጋት ስለሚያስፈልግ ግቢ ጉባኤያትን ማጠናከር ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር በመሆኑ በአንድ ሳምንቱ የገንዘብ ማሰባሰብ የግቢ ጉባኤ ባለአደራዎች የተጣለባችሁን ኃላፊነት እና አደራችሁን ተወጡ።
ልደታ ለማርያም
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ለከበረው ጤንነታችሁ እንዴት አላችሁ? ትምህርት እንዴት ነው? እየበረታችሁ እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን? በርቱ! ዛሬ የምንነጋራችሁ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደት ይሆናል!መልካም ንባብ!
“በክፉዎች መንገድ አትሂድ” (ምሳ.፬÷፲፬)
እግዚአብሔር መላእክትንና የሰው ልጅን ሲፈጥር የፈጠረበት ትልቁ ዓላማ ስሙን ቀድሰው ክብሩን እንዲወርሱ ነው፤ ነገር ግን ክፋትን ኃጢአትን ዲያብሎስ (አስቀድሞ ሳጥናኤል የተባለ) ከልቡ በሐሳቡ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለመ መላእክት አመነጫት፤ አመንጭቶም አልቀረም፤ ከራሱ ጋር ሌሎች እርሱን የመሰሉ መናፍስትን (መላእክትን) ይዞ ከሰማያዊ ክብሩ ወደቀ::