«ተዋሕዶ ለአንድሮይድ» የተሰኘ የስልክ ላይ አገልግሎት ተጀመረ
የካቲት 17 ቀን 2006 ዓ.ም.
በዝግጅት ክፍሉ ሪፖርተር
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ ማእከል ሚድያና ቴክኖሎጂ ክፍል «ተዋሕዶ ለአንድሮይድ» የተሰኘ የቴሌፎን አገልግሎት መስመር ዘረጋ፡፡ አገልግሎቱ በተለይ የእጅ ስልካቸው ወይም የኪስ ኮምፒዩተራቸው /ታብሌት/ አንድሮይድ በተሰኘው ግብረ ቴክኖሎጂ /ኦፕሬቲንግ ሲስተም/ አማካይነት የሚሠራ ምእመናን በያሉበት ኾነው በቀላሉ ልዩ ልዩ ትምህርቶችን፣ መዝሙራትን፣ የዕለትና የበዓላት ንባባትን /ግጻዌን/፣ በድምጽና በምስል የቀረቡ መንፈሳዊ ትረካዎችንና ጭውውቶችን፣ ልዩ ልዩ የጸሎት መጻሕፍትን እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ በልዩ ልዩ ግዛቶች ስለሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መረጃዎችን በቀላሉ እንዲያደርስ ኾኖ የተዘጋጀ ነው፡፡
- Google play – https://play.google.com/store/
apps/details?id=com.MkUs. tewahedo - App Store(iphone) – https://itunes.apple.com/us/
app/tewahedo/id720274202
ክፍሉ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ እንዳሳወቀው ቀደም ሲል ተመሳሳይ አገልግሎት አይ ፎንን መሠረት በማድረግ ሲጀምር ለምእመናን ቃል በገባው መሠረት፤ አገልግሎቱ በአንድሮይድ ግብረ ቴክኖሎጂም ይሰፋ ዘንድ የጀመረው መኾኑን ገልጿል፡፡
ይህንን አገልግሎት ለማግኘት የሚሹና አንድሮይድ የተሰኘውን ግብረ ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ የእጅ ስልክ ወይም የኪስ ኮምፒዩተር ያላቸው ሁሉ አገልግሎት ማግኛ መንገዱን /አፕሊኬሽኑን/ ከጎግል ፕሌይ ውስጥ ተዋሕዶ ከሚለውን የአገልግሎት ማዕቀፍ በመጫን መጠቀም እንዲችሉ ክፍሉ በአክብሮት ጋብዟል፡፡ ምእመናን ይህንን ጠቃሚ አገልግሎት ላልሰማ በማሰማት እንዲተባበሩም ጠይቋል፡፡