“ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አባቴ ነህ!”
መኮንኑ አፈረና ጽኑ ሥቃይ ሊያሠቃያቸው ወድዶ እንደ ክረምት ነጎድጓድ ድምፅ ወደ ሚያስተጋባው የፈላ ውኃ እንዲጥሏቸው አዘዘ፤ ያን ጊዜ እናቱ ፈራች፤ ሕፃኑ ግን ለእናቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እንዲህም አላት፤ “እናቴ ሆይ አትፍሪ! ጨክኝ፤ አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ እኛንም ያድነናል” አላት። እናቱ ቀና ብላ ብትመለከት ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁትን የብርሃን ማደርያቸውን ተመለከተች፤ ደስም ተሰኝታ እንዲህ አለች፤ “ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አባቴ ነህ፤ እኔም ልጅህ ነኝ፤ አንተን የወለድኩባት ቀን የተባረከች ናት፡፡”