“መባዬን በመያዝ ወደ ቤትህ እገባለሁ” (መዝ.፷፭፥፲፫)
ድንቅ በሆነ ሥራው ዓለምን ከእነ ጓዟ ለፈጠረ አምላክ የሚበቃ ከሰው ዘንድ የሚሰጥ ምን ነገር ይኖራል? ሰማይና ምድርን ለፈጠረ ባለ ጸጋው አምላካችን ልናቀርብስ የምንችለው ከእኛ የሆነ ከእርሱ ዘንድ ዋጋ ያለውስ ነገር ምን ይሆን? እርሱ ባወቀና በፈቀደ ከእርሱ የሆነ ግን ከእኛ የሚሰጥ ለአምላካችን ለልዑል እግዚአብሔር ስጦታን እንድናቀርብ ግን ተሰጠን፡፡ “ለከበረ ስምህም ከአንተ የተገኘውን ዕጣን አቀረብንልህ” እንዲል፡፡ ሁሉ በእጁ ለሆነው አምላክ ስጦታ እንድናቀርብም ክቡር ፈቃዱ ሆነልን፡፡