ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን? በተለምዶ የሰኔ ጾም እየተባለ የሚታወቀው ጾመ ሐዋርያት ሰኔ ፲፯ (ዐሥራ ሰባት) ቀን ተጀምሮ እስከዚህ ዕለት ደርሷል፡፡ ይህ ጾም ከሰባቱ የዐዋጅ አጽዋማት አንዱ ሲሆን አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት የመንፈስ ቅዱስ ጸጋን ከተቀበሉ በኋላ አገልግሎታቸውን በጸሎትና በጾም ጀምረዋል፤ እኛም እነርሱን አብነት አድርገን በዓለ ጰራቅሊጦስ ከተከበረበት ማግሥት አንሥቶ እስከ ሐምሌ አራት ቀን ድረስ እንጾመዋን፡፡ከዚያም በኋላ ሐምሌ አምስት ቀን የጾሙ ፍቺ ይሆናል፡፡ በዚህም ቀን የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስ የዕረፍት በዓል ነው፡፡
መልካም ልጆች! አሁን ለዛሬ ወዳዘጋጀንላችሁ ትምህርት እናምራ! ባለፈው ምሥጢረ ቁርባንን ተምረን ነበር፤ ዛሬ ደግሞ የምሥጢረ ትንሣኤ ሙታንን ትምህርት እንማራለን፡፡ ተከታተሉን!