በንባብ ባሕል ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሑፎች ይቀርባሉ
ሰኔ 23 ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
የንባብ ባሕልን ለማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሑፎች በማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ማእከል አዘጋጅነት ሰኔ 28 ቀን 2006 ዓ.ም ከ8፡00-11፡00 ሰዓት በማኅበሩ ሕንፃ ላይ እንደሚቀርቡ ማእከሉ አስታወቀ፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሁራን የሚቀርቡት ጥናታዊ ጽሑፎች ሁለት ሲሆኑ፤ “ትርጉም ያለው የንባብ ባሕል”፤ እንዲሁም “የንባብ ባሕልን ለማሳደግ የተለያዩ አካላት ሚና” በሚሉ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚያረጉ የጥናትና ምርምር ማእከሉ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሰይፈ አበበ ገልጸዋል፡፡
ትርጉም ያለው ንባብ ምንድን ነው? የንባብ ባሕልን ያሳደጉ አገራት ልምድ ምን ይመስላል? የንባብ ልምድ በሀገራችን እና በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ምን እንደሚመስሉ በጥናቶቹ ይዳሰሳሉ፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ማእከል በየዓመቱ በሀገራችን የንባብ ባሕልን ለማበረታታት ከሚያዘጋጀው የመርሐ ግብር አካል አንዱ ሲሆን፤ ጥናቶቹም የንባብ ባሕላችን ምን ላይ እንደሚገኝ የሚዳስሱና የሚያነብ ትውልድን ለመፍጠር ምን መደረግ እንዳለበት የሚያመላክቱ መሆናቸውን አቶ ሰይፈ ጠቁመዋል፡፡
ይህ የንባብ ጉባኤ ለሦስተኛ ጊዜ የተዘጋጀ ሲሆን፤ በመርሐ ግብሩ በንባብ ባሕል ላይ የሚሠሩ አካላት፣ ምሁራን፤ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት፤ እንዲሁም ምእመናን ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡




የደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም ያጋጠሙትን በርካታ ችግሮች ለመታደግ ዘላቂ መፍትሔ መሻት እንደሚገባ ሰኔ 8 ቀን 2006 ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ በተካሔደ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ጥሪ ቀረበ፡፡
ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገዳሙ ያለበትን ችግር አስመልክቶ ሲገልጹ “የደብረ ሊባኖስ ገዳም የኢትዮጵያዊያን ሁሉ ገዳምና ሀብት ነው፡፡ ገዳምነቱን ሊሸረሽሩ የሚችሉ በርካታ ችግሮች አጋጥመውታል፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመፍታትና የአባቶች የጸሎት ቦታ ተጠብቆ እንዲቆይ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ ስለሆነ ምእመናን ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል” ብለዋል፡፡
ግንባታ በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ያስረዳሉ፡፡ ምእመናን ይህንን በመረዳት የታቀዱት ፕሮጀክቶች ጊዜያቸውን ጠብቀው እንዲተገበሩም የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም በ2004 ዓ.ም. በገዳሙና በማኅበረ ቅዱሳን ባለሙያዎች ተጠንቶ የቀረበው የገዳሙ ሁለንተናዊ የልማት ፕሮጀክት ተግባራዊ በመሆን ላይ እንደሚገኝ የገዳሙ የልማት ኮሚቴ ገለጸ፡፡
የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ አብርሃም በግንቦት ወር 2006 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት የምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው በመዛወራቸው አዲሱን መንበረ ጵጵስና ተረክበዋል፡፡
ከግንቦት 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ቀናት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ሲካሔድ የቆየው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሀገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት 3ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ሰኔ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡
ጉባኤው በመጨረሻ ቀን ውሎው በየአኅጉረ ስብከቱ የሚታዩ እንቅስቃሴዎችንና ችግሮች አስመልክቶ ተሳታፊዎቹ በቡድን ውይይት በማድረግ ለጉባኤው አቅርበዋል፡፡ የግጭት አፈታት ዘዴን አስመልክቶ በመምህር በለጠ ብርሃኑ ጥናታዊ ጽሑፍ የቀረበ ሲሆን፤ በቀጣይ አንድ ዓመት ተፈጻሚ የሚሆኑ እቅዶች ላይ ውይይት ተካሒዶባቸዋል፡፡
