ቅዱስ መስቀል

ቅዱስ መስቀል ቀስት ከተባለ ጠላታችን ዲያብሎስ እንድናመልጥና ድል እንድናደርገው የተሰጠን ነው፤ ቅዱስ መስቀል መድኅን ዓለም ክርስቶስ ተሰቅሎ በክቡር ደሙ ቀድሶ የሰጠን፣  ሰላማችን የታወጀበት ኃይላችን፣ የሰላም አርማችን ነው!

የቤተ ክርስቲያን በዓላት አከባባር

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ አሸጋግሮ በሰላም ለዚህ ዕለት አደረሳችሁ! ዕንቁጣጣሽ እንዴት አለፈ? መቼም ደስ ብሏችሁ እንዳሳለፋችሁ ተስፋችን ነው!ልጆች! በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በዓላት እንዴት እንደሚከበሩ እኛም ደግሞ በምን ዓይነት መልኩ በበዓላት ላይ መሳተፍ አንዳለብን ልንነግራችሁ ወደድን፤ መልካም ቆይታ!

የምእመናን ድርሻ በቤተ ክርስቲያን ከምን ይጀምራል?

ቤተ ክርስቲያን የሁላችንም ቤት ናት፡፡ በቤታችን ሁላችንም የሥራ ድርሻ እንዳለን ሁሉ በመንፈሳዊት ቤታችን በቤተ ክርቲያንም እንዲሁ ሁላችንም ድርሻ ሊኖረን ይገባል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የሊቀ ጳጳሳት፣ የካህናት እና በቤተ ክርስቲያን በአስተዳደር ሥራ ላይ የተሠማሩ ሰዎች ቤት ብቻ ሳትሆን የሁላችንም ቤት ናት፡፡

እስራት

ሰዎች በልዩ ልዩ ምክንያቶች በወኅኒ ቤት ይታሰራሉ፡፡ አንዳንዶች ወንጀል ፈጽመው፣ ያልታረመ ንግግር ተናግረው፣ በማታለል ተግባር ተሰማርተው፣ ሴት አስነውረው፣ ቤት ሰርስረውና የመሳሰሉትን እኩይ ተግባራትን ፈጽመው ሊሆን ይችላል፡፡ የሰው ልጆችም በሲኦል ወኅኒ ቤት ተጥለን ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመናት ስንሠቃይ የነበረው አባታችን አዳም ትእዛዘ እግዚአብሔርን ጥሶ፣ አምላክነትን ሽቶ፣ አትብላ የተባለውን በመብላቱ ነበር፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ይህን አስመልክቶ ሲናገር ‹‹በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩት ነፍሳት ሰበከላቸው›› ይላል፡፡ (፩ኛጴጥ.፫፥፲፱)

ዳግም ሥራኝ!

የጽድቅ አበባዬ ጠውልጎ የኃጢአት ችግኜ አፈራ

አዝመራው ለምልሞ በለሱም የጎመራ

ለዓለም ሳጎበድድ  ጊዜዬን የጨረስኩ

በኃጢአት ብል ተበልቼ ባዶ ሆኜ የቀረሁ

ክርስትናዬን በነጠላ የሸፈንኩ

የራሴ ምሶሶ  እያለ ጉድፍ ለማውጣት የሮጥኩ

እኩይ ግብሬ ጸጽቶኝ በንስሓ ያልታጠብኩ

ርእሰ ዐውደ ዓመት

የዘመናት አስገኝ፣ የፍጥረታት ባለቤት፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ዓመታትን በቸርነቱ የሚያፈራርቅ፣ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ  በቸርነቱ አሻግሮናልና ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን!

በዓለ ቅዱስ ሩፋኤል

በዓለ ቅዱስ ሩፋኤል በጳጉሜን ሦስት ቀን የሚዘከር በዓል ነው፡፡ “ሩፋኤል” የሚለው ስያሜ ትርጉም “ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ” ማለት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከዕብራይስጥ ሁለት ቃላት ጥምረት የተገኘ ቃል ነው፡፡ “ሩፋ” ማለት ጤና፣ ፈውስ፣ መድኃኒት ማለት ሲሆን “ኤል” ሚለው በሌሎቹም መላእክት ስም ላይ የሚቀጸል ስመ አምላክ ነው::

“ተዘጋጅታችሁ ኑሩ’’ (ማቴ.፳፬፥፵፬)

ጌታች አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ደቀ መዛሙርቱ የነገራችው ኃይለ ነው፤ ‘’ጌታችሁ በምን ሰዓት እንደሚመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ፤ እወቁ ባለቤት ሌሊት ሌባ በየትኛው ጊዜ እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ በነቃ፤ ቤቱንም እንዲቆፈር ባልተወ ነበር’’ አላቸው፡፡ ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፤ የሰው ልጅ በማታስቡት ሰዓት ይመጣልና፤

ወርኃ ጳጉሜን

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? ጾመ ፍልሰታ እንዴት አለፈ? መቼም ደስ ብሏችሁ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ፣ በመማርና በማስቀደስ እንዳሳለፋችሁ ተስፋችን ነው፤ ልጆች! አሁን ደግሞ የዚህን ዓመት የመጨረሻ የሆነውን ጽሑፍ ስለ ‘ወርኃ ጳጉሜን’ ጥቂት ልናካፍላችሁ ወደድን፤ መልካም ቆይታ!

“ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር” (መዝ.፻፲፭፥፭)

ተክለ ሃይማኖት ማለት የስሙ ትርጓሜ “የሃይማኖት ተክል ማለት” ነው። ተክል ሥርም፣ ግንድም፣ ቅጠልም፣ ቅርንጫፍም ነውና ተክለ ሃይማኖት እንጂ ሌላ አላላቸውም። በእርሳቸው ተክልነት ቅርንጫፍ የሆኑ ፲፪ ከዋክብት አሉና “ተክል” አላቸው። ተክል ባለበት ልምላሜ አለ፤ እርሳቸው ባሉበትም የኃጢአት ፀሐይ፣ የርኩሰት ግለት የለም፤ የጽድቅ ዕረፍት እንጅ። ተክል ሕይወት ያለው ነገር ሁሉ ተደግፎት ይኖራል! ቢቆርጡት ለመብል ለቤት መሥርያ ይሆናል፤ ቢያቆዩት ማረፊያ መጠለያ ይሆናል፤ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም በዐጸደ ነፍስ ሆነው በምልጃ በጸሎት ያግዛሉ፤ ያማልዳሉ፤ በሕይወት ሳሉም በትምህርታቸውና በተአምራታቸው ኃይል ለብዙዎች ዕረፍት ሰጥተዋል።