የቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ካርታ
ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች! እንደምን ሰነበታችሁ? የጊዜ ባለቤት አምላካችን ክብር ምስጋና ይድረሰውና ዳግም አገናኝቶናል! በመጀመሪያው ክፍል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የመጭው ዐሥር ዓመታት የመንፈሳዊ እና ዘላቂ ልማት ግቦችን ማስተዋወቅን ዓላማ አድርገን ስለ ዕቅድ በጥቅሉ አቅርበንላችሁ ነበር፡፡ በዚህ ክፍለ ጽሑፍ ደግሞ ስለ መሪ ዕቅዱ ይዘቶች በጥቂቱ ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡