ልዩ ዐውደ ጥናት
ለአንተ እንዲደረግልህ የምትፈልገውን ለሌላውም አድርግ
ሰዎች በኑሮአቸው ሁልጊዜ እንዲፈጽሟቸው በቅዱስ መፅሐፍ ከተቀመጡ መንፈሳዊ ተግባራት ውስጥ፡
- የተራበን ማብላት፣
- የተጠማን ማጠጠት፣
- የታረዘን ማልበስ
- በአጠቃላይ ለሰዎች ሁሉ በጎ ነገርን ማድረግ ናቸው፡፡
ይህን የተቀደሰ ነባር መንፈሳዊ ተግባር አጠናክሮ ለመቀጠል እና የተቸገሩ ወገኖቻችን ለመርዳት፣ “ለአንተ እንዲደረግልህ የምትፈልገውን ለሌላውም አድርግ” በሚል ርእስ በችግር ላይ ያሉ ወገኖቻችን ማኅበራዊ ህይወት ለመደገፍ እና ራሳቸውን ችለው ህይወታቸውን መምራት እንዲችሉ ለማድረግ የሚያስችል ሲፖዚየም ተዘጋጅቷል፡፡
በሲንፖዚየሙ ላይ
- በማኅበራዊ ዘርፍ ከፍተኛ አገልግሎት ከሚሰጡ ተቋማት ተሞክሮ ይቀርባል፡፡
- በሁለት ልብሶች መርሐ ግብር ድጋፍ የተደረገላቸው አካላትን አስመልክቶ በፊልም የተደገፈ መረጃ ይቀርባል፡፡
- በማኅበራዊ ዘርፍ ጥናትና ምርምር ያደረጉ ሊቃውንት ልምዳቸውን ያካፍላሉ፡፡
አዘጋጅ፡-በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን
ቦታ፡- በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ
ቀን፡- ታህሣሥ 22 ቀን 2004 ዓ.ም
ስዓት፡-7፡30-11፡00
ስልክ 011 1 55 36 25