ልደቱ ለቅዱስ ማርቆስ

ቅዱስ ማርቆስ ትውልዱ ዕብራዊ ነው፤ ቤተሰቦቹ ግን ይኖሩ የነበሩት በሰሜን አፍሪካ ሲረኒካ  (ቀሬና) በተባለችውና በዛሬዋ ሊቢያ ምዕራባዊ ጠረፍ በተቆረቆረችው ደማቅ ነበር፡፡ ነገር ግን የሰሜን አፍሪካ  ዘላን ጎሳዎች የሆኑት በርበሮች በየጊዜው በከተማዋ ጥቃት እየነሰዘሩ ሀብት ንብረታቸውን እየዘረፉ ስላስቸሯቸው እናቱ ማርያምና አባቱ አርስጦቡሎስ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ኢየሩሳሌም በመመለስ ቤት ሠርተው ተቀመጡ፡፡…

አማኑኤል- እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ

ነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹እነሆ ድንግል በድንግልና ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች›› በማለት ትንቢት እንደተናገረው የተስፋው ቃል ይፈጸም ዘንድ በዘመነ ሥጋዌ እግዚአብሔር ወልድ ከንጽሕተ ንጹሐን ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ እንደሚወለድ መልአኩ እንዲህ ሲል አበሠራት፤ ‹‹እነሆ ትፀንሻለሽ፤ ስሙንም አማኑኤል ትይለዋለች፤  አማኑኤል  ማለት  እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።›› (ኢሳ.፯፥፲፬፣ማቴ.፩፥፳፫)

ቸሩ እረኛዬ

ሰላምን ስሻ በአንተ አምኜ
በጭንቅ በነበርኩበት እጅጉን አዝኜ
በዚህች በከንቱ ዓለም በጨለማ ሆኜ
ፈጥነህ ደረስክልኝ ሆነኸኝ አጽናኜ

‹‹እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም›› (ዘዳ. ፴፫፥፳፮)

ከጠፈር በላይ ርቀቱ፣ ከባሕር በታች ጥልቀቱ፣ ከአድማስ እስከ ናጌብ ስፋቱ የማይታወቅ፣  ነፋሳት ሳይነፍሱ፣ አፍላጋት ሳይፈሱ፣ ብርሃናት ሳይመላለሱ፣ የመባርቅት ብልጭታ ሳይታይ፣ የነጎድጓድ ድምጽ ሳይሰማ፣ መላእክት ለቅዳሴ ከመፈጠራቸው አስቀድሞ፣ በአንድነቱ ሁለትነት፣ በሦስትነቱ አራትነት ሳይኖርበት፣ ለቀዳማዊነቱ ጥንት፣ ለማዕከላዊነቱ ዛሬ፣ ለደኃራዊነቱ ተፍጻሜት የሌለበት፣ በባሕርዩ ሞት፣ በሥልጣኑ ሽረት፣ በስጦታው ንፍገት የማይስማማው፣ የማይሾሙት ንጉሥ፣ የማይጨበጥ እሳት፣ የማይነጥፍ የፍቅር ጅረት፣ የነበረ ያለና የሚኖር፣ እንደ አምላካችን እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም፡፡