ጸሎትና ጥቅሙ
ልጆች ትምህርት ጥሩ ነው?ቤተ ክርስቲያን እሑድ እሑድ ትሔዳላችሁ ? በጣም ጥሩ ልጆች ! ዛሬ የምንማማረው ስለ ጸሎት ጥቅም ነው፡፡ ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር የምንገናኝበት እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት ትልቅ ኃይል ማለት ነው፡፡
በጸሎት የእግዚአብሔርን ሩህሩህነት፣ ቸርነት ኃያልነት እንገልጻለን፡፡ በጸሎት እግዚአብሔር ያደረገልንን ሁሉ አስታውሰን ምስጋና እናቀርባለን፡፡ በጸሎት በደላችንን ለእግዚአብሔር እንናዘዛለን፡፡ ይቅርታውንም እንጠይቃለን፡፡ በጸሎት ከእግዚአብሔር የፈለግነውንና የጐደለንን ለማግኘት እንለምናለን፡፡ ጸሎት ይቅርታ መጠየቂያ በመሆኗ ከቅጣትና ከመከራ የምታድን ናት፡፡ እንግዲህ ልጆች በአጠቃላይ የጸሎት ጥቅም ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡ ልጆች እናንተስ ጠዋት ከመኝታችሁ ስትነሡ ማታ ስትተኙ ትጸልያላችሁ ?
ወይንስ ዝም ብላችሁ ትተኛላችሁ፡፡ ትነሣላችሁ? ማታ ስትተኙ እግዚአብሔርን አመስግናችሁ ጠዋት ስትነሡ እግዚአብሔርን አመስግናችሁ ጸልያችሁ መዋል አለባችሁ፡፡ ልጆች ምግብም ስትመገቡ ጸሎት አድርሳችሁ መመገብ አለባችሁ፡፡ ልጆች ጸሎት ትምህርታችሁን ይገልጽላችኋል፡፡ ከብዙ ክፉ ነገር እግዚአብሔር ይጠብቃችኋል፡፡
እንግዲህ ልጆች ጸሎት ብዙ ዓይነት ነው፡፡ 1ኛ የግል ጸሎት፣ 2ኛ. የማኅበር ጸሎት 3ኛ. የቤተሰብ ጸሎት አለ፡፡ ስትጸልዩ በጸጥታና ካለወሬ መጸለይ ያስፈልጋችኋል፡፡ በአጠቃላይ የጸሎትን ጥቅም ማወቅ ይገባናል፡፡ እሺ ልጆች! ከብዙ በጥቂቱ የጸሎትን ጥቅም እንዳወቃችሁ ተስፋ እናደርጋለን፡፡