የቱን ታስታውሳላችሁ?
ዲያቆን ተስፋዬ ቻይ
ታኅሣሥ ፲፬፤፳፻፲፯ ዓመተ ምሕረት
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን? ትምህርት እንዴት ነው? እየበረታችሁ ነውን? የምትማሩትን ትምህርት እያጠናችሁ እንደሆነ ተስፋችን ነው፤ በርቱ! ልጆች ለዛሬ ይዘንላችሁ የቀረንበው ባለፉት በተከታታይ ሳምንታት ስንማማረው ከነበረው የአማላጅነት ትምህርት ካነበበችሁት (ከተማራችሁት) መካከል “የቱን ታስታውሳላችሁ” በሚል ርእስ ጥያቄዎችን ነው፡፡ በጥንቃቄ አንብባችሁ መልሶቻችሁን በድረ ገጽ አድራሻችን “website.amharic@eotcmk.org” እና “https://t.me/Hiwot122716” ትልኩልናላችሁ!
ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልሶች ምረጡ!
……፩. የቅዱሳን አማላጅነት ያስፈለገበት ምክንያት ———————–ነው፡፡
ሀ. እግዚአብሔር ከኃጥአን-ጸሎት ይልቅ የወዳጆቹ የቅዱሳንን ጸሎት ስለ ሚቀበል
ለ. ጸሎታችን በፍጥነት ወደ እግዚአብሔር እንዲደርስልን
ሐ. ፈጣሪያችንም ስለ እነርሱ ሲል ቸርነቱን ስለሚያደርግልን ነው፡፡
መ. ሁሉም መልስ ነው
…… ፪. በአማላጅነት ተግባር ውስጥ መኖር ያለበት ———————–ነው፡፡
ሀ. አማላጅና የሚማለድለት ብቻ ለ.ተማላጅ
ሐ. ሀ እና ለ መልስ ናቸው፡፡ መ. መልሱ የለም
…… ፫. ለተጠማ ሰው ውኃ አጠጥቶ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያማለደችውና ከመከራ የታደገችው ሰው ማን ይባላል?
ሀ. አብርሃም ለ. ነዌ
ሐ. አልአዛር መ. ስምዖን ( በላዔ ሰብእ)
…… ፬. ለእግዚአብሔር ቅድስናው——————
ሀ. የጸጋ ነው ለ. የባሕርይ ገንዘቡ ነው
ሐ. ከማንም ያልተቀበለው ነው መ. ለ እና ሐ መልስ ናቸው
……፭. ‹‹…በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ …›› (፪ኛ ቆሮ. ፭፥፲፱) የሚለው ኃይለ ቃል ምንን ያመለክታል፡፡
ሀ. የቅዱሳንን አማላጅነት ለ. አማላጅነትን የፈቀደው እግዚአብሔር እንደሆነ
ሐ. አማላጅ እንደማያስፈልግ መ. ሀ እና ለ
ለሚከተሉት ጥያዌዎች ትክክለኛውን ምላሽ ጻፉ!
፮. እመቤታችን ከልጇ አማልዳ ውኃውን ወደ ወይን ጠጅ ጌታችን የቀየረበት ቦታ ምን ይባላል?
……………………………………………………………………………………………………
፯. አማላጅ ማለት ምን ማለት ነው? ቅዱሳን ያማልዳሉ ስንል ምን ማለት ነው? ይህንን ከተማራችሁት በአጭሩ አብራሩ!
……………………………………………………………………………………………………
፰. የቅዱሳን አማላጅነት ያስፈለገበት ምክንያት ምንድን ነው?
……………………………………………………………………………………………………
፱. የቅዱሳንን በዐጸደ ሥጋ አማላጅነትን ከተማራችሁት ጠቅሳችሁ ጻፉ!
……………………………………………………………………………………………………
፲. አቤሜሌክ የተባለን ሰው እግዚአብሔር በሕልሙ ተገልጾ ጥፋት እንዳያጠፋ፣ ሊሠራ ስላሰበው በደል ግን ‹‹…ነቢይ ነውና ስለ አንተም ይጸልያል፤ ትድናለህም..›› በማለት ወደ እግዚአብሔር ጸልዮ ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ መሥዋዕትን ወደ እግዚአብሔር አቅርቦለት በደሉ ይቅር እንዲባል ያደረገ ቅዱስ ማን ነው? ……………………………………………………….
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እስከ አሁን ድረስ ስለ አማላጅነት ቀርቦ ከነበረው ብዙ ትምህርት “የቱን ታስታውሳላችሁ?! በሚል ርእስ ጥቂቱን ብቻ ጠየቅናችሁ፤ ምላሻሁን እንጠብቃለን፡፡
አምላካችን እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር ልዩ ነውና ውለታውን ሳንረሳ ትእዛዙን በመጠበቅ ለእርሱ ያለንን ፍቅር እንግለጽ፡፡ ወላጆቻችን ለእኛ ብዙ ነገር በማድረግ በትምህርታችን ጎበዝ ስንሆንና በሥነ ምግባር ስንታነጽ ደስ እንደሚላቸው ሁሉ እኛም ፈጣሪ እግዚአብሔር ያዘዘንን ትእዛዝ በመፈጸም ለእርሱ ያለንን ፍቅር እንግለጽ፡፡
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! በቀጣይ በሌላ ትምህርት እንገናኛለን! መልሶቻችሁን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ተከታታይ ዐሥር ቀናት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ መላካችሁን እንዳትረሱ፤ ቸር ይግጠመን!!!
ስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!