===== ዜና ሐዊረ ሕይወት ======
ዝግጅቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየተከናወነ ሲሆን የትኬት ሥርጭቱም በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡
ደብረ ኤዶም ቅዱስ ገብርኤል፡-
የእግር መንገድ? መኪና እስከ ቤተክርስቲያኑ የሚደርስ በመሆኑ የእግር መንገድ አይኖረውም፡፡ ይህም የዐቅም እና የጤና ችግር ላለባቸው ጥሩ ዜና ነው፡፡\
የመኪና ማቆሚያ? እስካሁን ከተደረጉት ጉዞዎች ከ100 በላይ መኪና ሊያስተናግድ የሚችል ሰፊና ውብ የሆነ ቦታ እንዳለው ተረጋግጧል፡፡
የተዘጋጁ ትኬቶች ስንት ናቸው? የተጓዥ ብዛትስ?
5000 ቲኬቶች ተዘጋጅተዋል(ካለፈው ዓመት በአንድ ሺህ ቁጥር ጭማሪ ይኖረዋል)፡፡በመሆኑም በዚህ ጉዞ ከአስተናጋጆች ጋር ከ5500 በላይ ተሣታፊዎች እነደሚኖሩ ይጠበቃል፡፡
የትኬት ሥርጭት፡- የተዘጋጁት ትኬቶች ውስጥ 4800 በላይ ትኬቶች ከአዘጋጅ ኮሚቴው እጅ የተሰራጩ ሲሆን ሽያጩም ካለው ጊዜ አኳያ በሚያስገርም ሁኔታ በፍጥነት በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ስንት አሰተናጋጆች ይኖራሉ? ይህን ጉዞ ስኬታማ ለማድረግ ከአበው ጸሎት ጋር ትኬት በመሸጥ ፣ በምግብ ዝግጅት፣ በመኪና ላይ መስተንግዶ፣ በመዝሙር ፣በሕክምና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ኤሌክትሪክ፣ጽህፈት እና ሌሎችም ከ400 በላይ አገልጋዮች ይኖራሉ፡፡
ትኬቱ የት ይገኛል? በማስታወቂያ በተገለጹበት ቦታዎችና እንዲሁም በየወረዳ ማእከላቱ ይገኛል፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ በማኅበሩ ሕንጻ ላይ የሚሸጠው ትኬት ይጠናቀቃል፡፡
ምን ዝግጅቶች አሉ?
ድንኳን፡– ከ5000 – 6000 ሰው የሚይዝ ድንኳን ይዘጋጃል፡፡
ጀኔሬተር፡– መብራት ቢጠፋ ለመጠቀም የሚያስችል ጀኔሬተር ይኖራል፡፡
ሕክምና፡- በጉዞው ላይም ሆነ በቦታው ለሚፈጠሩ የጤና ችግር ልዩ የሕክምና ቡድን ከአስፈላጊ መድሃኒቶችና የሕክምና መሳሪያ ጋር ይኖራል፡፡
ቀጥታ ሥርጭት፡- ሥርጭቱ በመላው ዓለም ለሚገኙ ምዕመናን ከስፍራው በቀጥታ ለማስተላለፍ ዝግጅት ይደረጋል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ከአ.አ ውጭ ያሉ ተጓዦች ከወዲሁ ትኬት ሣያልቅ እንዲመዘገቡ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
ባለፈው ዓመት ከአ.አ ውጭ ከሰንዳፋ፣ ወሊሶ፣ አምቦ፣ ጅማ፣ ደ/ዘይት፣ ሞጆ፣ ባህር ዳር፣ መቀሌ፣ ደሴ፣ አፋር አዳማ(ናዝሬት)በርካታ ተጓዦች እነደነበሩ ይታወሳል፡፡
የአዘጋጅ ኮሚቴው ስጋት! በባለፉት ጉዞዎች እንደታየው ትኬቱ አስቀድሞ ስለሚያልቅ ትኬት ፈላጊ ምዕመናንን ማስተናገድ አለመቻል ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- በክርስቲያናዊ ሕይወትዎ እንዲመለስልዎት የሚፈልጉትን ማንኛውንም ጥያቄ በe-mail፡ hawirehiywot@yahoo.com አድራሻ ያቅርቡ፡፡ አባቶች በዕለቱ ከልምዳቸው በመነሳት መልስ ይሰጥዎታል፡፡ (hawirehiywot@yahoo.com)
ልብ ይበሉ! መረጃዎችን መከታተል ትኬቱን ይዞ ነው!
++++++ በጸሎትዎ ያስቡን! ++++++