በዓለ ደብረ ቁስቋም
ኅዳር ፭፤፳፻፲፮ ዓመተ ምሕረት
በከበረች በኅዳር ስድስት ቀን የምናስበው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደ ልጇ ከመድኃኒዓለም፣ ከአረጋዊው ዮሴፍ እና ሰሎሜ ጋር ከስደት መመለስ እንዲሁም በቁስቋም ተራራ መገኘት ታላቅ በዓል ነው፡፡
ዳግመኛም በዚህች ቀን በኋላ ዘመን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ቁስቋም ቅዱሳን ሐዋርያትን ሰብስቦ፣ ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንን አክብሮ፣ መሥዋዕትን ሠርቶ፣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ለወገኖቹ ሰጣቸው፡፡ የእስክንድርያ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቴዎፍሎስ ምስክሮች ሆነዋል፡፡
የአምላካችን ቸርነት፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ አሜን!
ምንጭ፡- መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ኅዳር