ማኅበረ ቅዱሳን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተረጎማቸውን “መጽሐፈ ግንዘት” እና ˝የዮሐንስ ወንጌል ቅጽ ሁለት” መጻሕፍትን አስመረቀ!

ጥቅምት ፲ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም

የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ መምህር ዋሲሁን በላይ ከዚህ ቀደም በርካታ መጽሐፍት ተጽፈው፣ ተተርጒመው፣ ታትመው ለአገልግሎት መዋላቸውን ገልጸው እነዚህን “መጽሐፈ ግንዘት” እና  ˝የዮሐንስ ወንጌል በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ  ቅጽ ሁለት”‌ መጻሕፍትን ግን ማኅበሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ማስተርጎሙን አሳውቀዋል፡፡

ጥቅምት ፰ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም  በዋናው ማእከል ሕንጻ ሦስተኛ ወለል ንቡረ እድ  ድሜጥሮስ አዳራሽ በተከናወነው መርሐ ግብሩ ላይ መጽሐፍቱ በአባቶች ተመርቀዋል፡፡  መጻሕፍቱን በመተርጎም ኃላፊነታቸውን ለተወጡ አካላትም የምስክር ወረቀትና ስጦታ ተሰጥቶአል።

በተጓዳኝ ዋና ሥራ አስፈጻሚው መጻሕፍቱ እዚህ እንዲደርሱ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋናን አቅርበዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት ሊቀ ሊቃውንት ዮሴፍ ደሳለኝ የሊቃውንት ጉባኤ አባልና  የአራቱ መጻሕፍት ጉባኤያት የትርጓሜ መምህር ደግሞ “መጽሐፈ ግንዘት” የተሰኘውን እንዲሁ መምህር ቀሲስ ዐቢይ ሙሉቀን የሐመር መጽሔት ምክትል ዋና አዘጋጅ ˝የዮሐንስ ወንጌል በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ  ቅጽ ሁለት”  በተመለከተ የመጽሐፍ ዳስሳ አድርገዋል።