መምህር ሆይ!

ሚያዚያ ፲፩፤፳፻፲፮ ዓመተ ምሕረት

መሆንህን አውቆ እውነተኛ

ገሰገሰ ወዳንተ በሌሊት ሳይተኛ

ቅዱስ ቃልህንም ሲሰማ ፈወሰው

የታወረ ኅሊናውን አብርቶ አቀናው

ጥያቄውን እንዲያቀርብ አበረታታኸው

ስለ ዳግም ውልደትም አስተማርከው

‹‹እውነት እውነት እልሀለሁ›› ስትለው

ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው…

የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይቻለው››

ምሥጢሩ ባይገባው

  •  

‹‹ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡

ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው››

ብለህ አስረዳኸው፡፡

‹‹ይህ ሊሆን እንዴት ይቻላል?›› ብሎ ኒቆዲሞስ ቢጠይቅህ

‹‹አንተ የእስራኤል መምህራቸው ነህ፤

ነገር ግን እንዴት ይህን አታውቅም?….

ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፤…

የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀል ዘንድ አለው፡፡››

ብለህ አስተማርከው፡፡

አሁንስ ገባው፤ እውነቱንም አውቆ ጌታውን

ዘመናት አልፈው ሲደርስ ጠብቆ ተራውን

ቢኖርም ተብሎ መምህር፣ በሌላ ሕግ ተደብቆ

ያለ አንተ ሲኖር ከአይሁድ ተደባልቆ

አሁን ግን ሰጠኸው የእውነት ሕይወት

በመስቀል ላይ ገልጸህ ፍጹም አፍቅሮት

ክብርንም አገኘ በአንተ ስቅለት

ገንዞ እንዲቀብርህ በዓርብ ዕለት!